🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር "ኢትዮጵያን የማገናኘት 75 ዓመታት፤ መንገዳችን ኃላፊነታችን" በሚል መሪ ሃሳብ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩን በዓል በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብሯል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ክብረ በዓሉ ስኬቶች በመዘከር የወደፊቱን ዘመናዊ የመንገድ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ግቦች የሚታደሱበት አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደርም ባለፉት 75 ዓመታት ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮጀክቶችን የመፈጸም ከፍተኛ አቅም እየገነባ የመጣ ተቋም መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀጣይም ጥራታቸውን የጠበቁ፣ ዘላቂ፣ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር የሚጣጣሙና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ያካተቱ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እድገት የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነባ መሆኑንም አስረድተዋል።
የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የመሠረተ ልማት ግንባታው በይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ሚኒስቴሩም ለአስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍና ክትትል አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥና የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የቦርድ ሰብሳቢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ አስተዳደሩ በ75 ዓመታት ጉዞው የሀገሪቱ ልማት ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን ከ180 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መድረሱን በመጠቆም፣ በቅርብ ዓመታት ብቻ ከ44 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች በመገንባት የዜጎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።
የመንገድ መሠረተ ልማት ሕዝቦችን ከማቀራረብ ባለፈ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት እያፋጠነ ነው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን ናቸው።

የኢትዮጵያ የመንገድ አውታር መስፋፋት ተቋማዊ የቴክኖሎጂ አቅምን ከማሳደጉም በተጨማሪ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለተቋሙ ስኬት መሠረት ለጣሉ የቀድሞ አመራሮች የመንገድ ፕሮጀክቶችን እውን ለማድረግ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መሐንዲሶች፣ ባለሙያዎችና ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026