የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከ118 ሺህ የሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል ተጠቃሚ ሆነዋል

Jul 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጭሮ ፤ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ118 ሺህ የሚበልጡ ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የዞኑ ስራ ዕድል ፈጠራ ጽህፈት ቤት ገለፀ።

የሥራ ዕድሉ ተጠቃሚዎችም በመንግሥት በተመቻቸላቸው የብድርና የማምረቻ ቦታ በመታገዝ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጽሕፈት ቤቱ የዕቅድ ዝግጅት እና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አሸብር ደበበ ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ ጽሕፈት ቤቱ በ8 ሺህ 801 ማኅበራት ለተደራጁ 118 ሺህ 500 ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።

ለዚህም ስኬታማነት የመሬት ዝግጅት፣ የብድር አቅርቦትና የስልጠና አገልግሎት በመስጠት ዜጎችን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል ብለዋል።

ከተፈጠረው የሥራ መስክ መካከል ግብርና፣ የእንስሳት እርባታና ማድለብ፣ ንብ ማነብ፣ የዶሮ እርባታ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድና ሌሎችም እንደሚገኙበት አመላክተዋል።

በእንቅስቃሴያቸው ውጤታማ እንዲሆኑም በገጠርና በከተሞች በ3 ሺህ 200 ማኅበራት ለተደራጁ ወጣቶች 4 ሺህ 335 ሄክታር የእርሻና የመስሪያ ቦታ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

የመነሻ ካፒታል እጥረት እንዳያጋጥማቸውም ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መንግሥት ማመቻቸቱን አስታውቀዋል።

ከወሰዱት ብድር ውሰጥ እስካሁን ድረስ ከ65 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆነው ተመላሽ ማድረግ መቻላቸውን ተናግረዋል።

ለምርቶቻቸውም ከተለያዩ ተቋማት እና ድርጅቶች 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተደራጅተው በዶሮ እርባታ የተሰማሩት አቶ አሰበ ተስፋዬ እንዳሉት፤ በተመቻቸላቸው የመስሪያ ቦታና ብድር በመታገዝ በመጀመሪያው ምዕራፍ 600 እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን እያረቡ ይገኛሉ።

አሁን ላይ የእንቁላል ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በቦኬ ወረዳ ቦኬ ጥቃ ከተማ በእንስሳት ማድለብ ከጓደኞቹ ጋር የተሰማራው ወጣት ሀብታሙ ዓለሙ በበኩሉ፤ ባገኙት 500 ሺህ ብር ብድር የመነሻ ካፒታል የጀመሩት ሥራ ውጤታማ እያደረጋቸው ይገኛል።

ሰንጋዎችን በማድለብ ከአካባቢው ገበያ ባለፈ ለጭሮ እና በዴሳ ሉካንዳ ነጋዴዎች በማቅረብ ትርፋማ መሆናቸውን ነው የገለፀው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026