🔇Unmute
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስፋፊያ እና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፥ ማስተር ፕላኑ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና ማሻሻያ ስርዓት ይበልጥ ዘመናዊ ፤አስተማማኝና በዲጂታል የተደገፈ ለማድረግ የተዘጋጀ ታሪካዊ ፍኖተ ካርታ ነው።

የአሰራር ስርዓቱ የምህንድስና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ሀገራዊ የልማት አጀንዳ መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም ማስተር ፕላኑ ለኢትዮጵያ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና የማህበራዊ ትራንስፎርሜሽን መሠረት እንደሚሆን ተናግረዋል።
በጥናቱ ሰነድ መሠረት፣የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ከፍተኛ ፍላጎት በፈረንጆቹ 2025 ካለበት 4 ሺህ 289 ሜጋ ዋት በ2049 ወደ 39 ሺህ 327 ሜጋ ዋት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ ዕድገት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር፣ ከከተሞች መስፋፋት፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ከኢ-ሞቢሊቲ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ መሆኑም ተጠቅሷል።
ይህንን ፍላጎት ለማሟላት እስከ 2049 ድረስ በሀገር አቀፍ ደረጃ 128 አዳዲስ ሰብስቴሽኖችን መገንባት ያስፈልጋል ተብሏል።
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026
አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...
Sep 3, 2026
ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...
Aug 12, 2026
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...
Aug 12, 2026