የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የ'ዌልመል' መስኖ ፕሮጀክት ግብርናውን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አቅም ፈጥሯል

Jul 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደሎ መና ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ የ'ዌልመል' መስኖ ፕሮጀክት የግብርና ሥራን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አቅም የፈጠረ መሆኑን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች ቡድን በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ ለአካባቢው ማኅበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን የ'ዌልመል' የመስኖ ፕሮጀክትን ጎብኝተዋል።


የመስኖ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን አርሶና አርብቶ አደሮች ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተመልክቷል።

ፕሮጀክቱ በመንግሥት ትኩረት በበጀት ዓመቱ ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃ ሲሆን፣ የአካባቢውን ማኅበረሰብ የመስኖ ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በመስክ ምልከታው ላይ የተገኙት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ፕሮጀክቶች ፕሮግራም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ሊካሳ እንዳሉት፣ በሀገሪቱ የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት የአርሶና አርብቶ አደሩን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።


በዚህም አርሶና አርብቶ አደሩ የተለያዩ የውኃ አማራጮችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መታየታቸውን አክለዋል።

በአርሶና አርብቶ አደሩ ማኅበረሰብ አካባቢ የዝናብ እጥረትና ድርቅ ለዜጎች ሕይወት ፈተና ሆኖ መቆየቱን የገለጹት አቶ አሸናፊ፤ በየአካባቢው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተከናወኑ አማራጭ የመስኖ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ኑሯቸውን እየለወጡ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ለዚህም በባሌ ዞን ደሎ መና ወረዳ የተገነባው የዌልመል የመስኖ ፕሮጀክት አንዱ ማሳያና ከዚህ በፊት በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሲረዱ የነበሩ አርሶና አርብቶ አደሮችን ከዝናብ ጥገኝነት በማላቀቅ በዓመት ሁለትና ሦስት ጊዜ በማምረት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስቻይ ሁኔታ መፍጠሩን አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የማልማት አቅም ያለውና ከ24 ሺህ በላይ አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

የደሎ መና ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኡመር መሐመድ በበኩላቸው፣ በወረዳው ሰፊ ሊለማ የሚችል የእርሻ መሬት ቢኖርም ከዝናብ እጥረት የተነሳ የአካባቢው ማኅበረሰብ የሴፍቲኔት ተረጂ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል።


በመንግሥት ትኩረት በዚህ ዓመት ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው የዌልመል መስኖ ፕሮጀክት አርሶና አርብቶ አደሩ በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ በማልማት ወደተሻለ የኑሮ ደረጃ እንዲሸጋገር እያገዘ መሆኑን ተናግረዋል።

የጎምጎማ ቀበሌ አርሶና አርብቶ አደሮች መካከል ኢስማኤል አማን በሰጡት አስተያየት፣ ቀደም ሲል እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች የአካባቢያቸው ነዋሪዎች በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ታቅፈው ሲረዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል።


የመስኖ ፕሮጀክቱ በመጠናቀቁ በ1 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ገበያ ተኮር ምርቶችን በማልማት ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅትም እያለሙ ካሉት ነጭ ሽንኩርት 2 ሚሊዮን ብር ገቢ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የዝናብ ወቅትን ብቻ በመጠበቅ በዓመት አንድ ጊዜ ያመርቱ እንደነበርና ኑሯቸውም ከእጅ ወደ አፍ እንደነበር ያስታወሱት ደግሞ ሌላው የመስኖ ተጠቃሚ አደም በያን ናቸው።


አሁን ላይ በመስኖ ፕሮጀክቱ በመጠቀም ምርት በስፋት እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።


አቶ አብዱላሂ ጅብሪል በበኩላቸው፣ የዌልመል መስኖ ፕሮጀክት ከሴፍቲኔት ጠባቂነት አላቆን በራሳችን እንድንቆም አግዞናል፤ በመስኖው በመታገዝ ሰብል እንዲሁም ገበያ ተኮር አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026