🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል።
የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል።
በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዘጋጅነት የተካሄደው የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል።
ሚኒስትሮቹ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ አጀንዳዎችና የአፍሪካን አህጉራዊ ትስስር ማፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በስብሰባው ሚኒስትሮቹ የአጀንዳ 2063 አፈፃፀም የሚከታተለውን ኮሚቴ ሪፖርት እንዲሁም የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና በአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ወቅት ያሉ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎች ያሉበትን የትግበራ ደረጃ ገምግመዋል።
በተጨማሪም የ2026ቱን የህብረቱን የዓመቱ መሪ ሀሳብ የእስካአሁን የአፈጻጸም ሂደት ላይም መክረዋል።
ስብሰባው እ.አ.አ. በ2017 በህብረቱ አባል ሀገራትና መንግስታት መሪዎች የፀደቀውን ተቋማዊ ማሻሻያ መነሻ ያደረገ ነው።
ከስብሰባው የተገኙ ውጤቶች አህጉራዊ ዘላቂ ልማትን፣ ትስስርና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የተቀረፀውን የአፍሪካ ህብረት የረጅም ጊዜ መሪ እቅድ (አጀንዳ 2063) ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስ...
Jul 28, 2026
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማ...
Jul 24, 2026
ጅማ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ በጅማ ዞን የሩዝ ሰብልን ለማስፋፋት በተከናወነው ሥራ ምርታማነቱ እያደገ መምጣቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገልጿል። በዞኑ...
Jul 22, 2026
ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ199 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 72 ኪሎ ሜትር የጠ...
Jul 18, 2026