የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የሲቪል ምዝገባ የዲጂታል ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ ነው

Aug 6, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የጀመረው ዲጂታል የአሰራር ስርዓት ዜጎች የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አሰራሩን ለማዘመንና ለማቀላጠፍ አገልግሎቶቹን በኦንላይን በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የኦንላይን አገልግሎቱ ገፅ ለ ገፅ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተሻለ ሁኔታ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው በሞባይል፣ በላፕቶፕና በሌሎች ዲጂታል መሳሪያዎች በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።


የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ንጉሤ ለኢዜአ እንደገለጹት ፤ ተቋሙ በአጠቃላይ ከሚሰጣቸው ሰባት ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል በአሁኑ ወቅት የመታወቂያ፣ የልደት እና ያላገባ ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በኦንላይን እየሰጠ ይገኛል።

እስከ አሁን ከ15 ሺህ በላይ ተገልጋዮች በኦንላይን ሥርዓቱ አገልግሎት ማግኘታቸውን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ አዲሱ አሰራር የተገልጋዮችን ጊዜና ወጪ ከመቆጠቡም በላይ እንግልትን እያስቀረ መሆኑን አስረድተዋል።

በተጨማሪም አሰራሩ ለባለሙያዎች ምቹ የሥራ ሁኔታ በመፍጠር የሥራ ቅልጥፍናንና ውጤታማነትን ማሳደጉን ገልጸዋል።

ኤጀንሲው መረጃዎችን በዲጂታል ሥርዓት በማደራጀት ዘመናዊ የኦንላይን አገልግሎቶችን በስፋት ተደራሽ የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።

በቀጣይም የጋብቻ፣ የፍቺ፣ የሞትና የጉዲፈቻ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሌሎችንም አገልግሎቶች ወደ ኦንላይን ሥርዓት በማስገባት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግ እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ከጤና ተቋማትና ከፍርድ ቤቶች ጋር በመቀናጀት እንደ ልደትና ሞት ያሉ ኩነቶች በተከሰቱበት ቦታ ላይ በቀጥታ እንዲመዘገቡ የሚያስችል አሰራር እየተጠናከረ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በኤጀንሲው እየተከናወነ ያለው ይህ የዲጂታል ሽግግር የኢትዮጵያን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ እና የከተማዋን የስማርት ከተማ ግንባታ ግብ እውን ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ በመገናኛ ብዙኃንና በተለያዩ አማራጮች ህብረተሰቡ ስለ ኦንላይን አገልግሎቱ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የ25 ዓመት የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እስከ ፈረንጆቹ 2049 ድረስ የሚተገበር የ25 ዓመታት ሀገር አቀፍ የኤሌክትሪክ ማስ...

Jul 28, 2026

የኢትዮጵያ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ መንገድ መሰረተ ልማቶች የሕዝብን የኢኮኖሚ ትስስር በማሳለጥ የብልፅግና ድልድይ እየገነቡ መሆኑን የከተማ...

Jul 24, 2026

በጅማ ዞን የሩዝ ምርታማነት እያደገ መጥቷል

ጅማ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ በጅማ ዞን የሩዝ ሰብልን ለማስፋፋት በተከናወነው ሥራ ምርታማነቱ እያደገ መምጣቱን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገልጿል። በዞኑ...

Jul 22, 2026

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ199 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጠጠር መንገዶች ተገንብተዋል

ደብረ ብርሃን ፤ ሐምሌ 10/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ199 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 72 ኪሎ ሜትር የጠ...

Jul 18, 2026