የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከልን ጨምሮ ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮችን ለመዘርጋት ተችሏል- ቢሮው

Aug 31, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፡ ነሐሴ 22/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከልን ጨምሮ ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮችን በመዘርጋት ቀልጣፋና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት መስጠት መቻሉን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው ባለፉት ሦስት ዓመታት በዲጂታላይዜሽን ትግበራ በተመዘገቡ ውጤቶችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬመግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የመሶብ አንድ ማዕከላትን ጨምሮ የተለያዩ ዘመናዊ መተግበሪያዎችን በማልማት ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተችሏል።

የክልሉ መንግሥት በ25 ዓመት የስትራቴጂክና አሻጋሪ ዕቅዱ ለቴክኖሎጂው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት መሠረት፣ አገልግሎት በሚበዛባቸው ተቋማት ላይ በማተኮር ከ35 በላይ የዲጂታል አሰራሮች መዘርጋቱን ነው የገለጹት።

ቴክኖሎጂዎቹ በፍትሕ ሥርዓት፣ በፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ ኢንቨስትመንት በመሳብና በግብርናው ዘርፍ ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማስቻላቸውንም አብራርተዋል።

በተጨማሪም ቴክኖሎጂዎቹ የመንግሥት አካላት በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲሰጡ ከማድረጋቸው ባሻገር፣ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አስረድተዋል።

በተለይም "መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በክልል ደረጃ በባህር ዳር፣ ደሴና ወልዲያ ከተሞች ተግባራዊ በማድረግ የህዝቡን እርካታ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።

በተካሄደው የዳሰሳ ጥናትም እስካሁን ከ103 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በኩል ፈጣን ፣ ፍትሐዊና ከብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት ማግኘታቸው መረጋገጡን አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅትም የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሌሎች ከተሞች ለማስፋት የግንባታና የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ሥራው እየተፋጠነ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በቀጣይ ዓመትም የዲጂታል 2030ን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ ከ13 በላይ አዳዲስ መተግበሪያዎችን የማልማት ስራ እንደሚከናወን አብራርተዋል።

በክልሉ በዲጂታል ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ለህዝብ ለማስተዋወቅ ያለመ የፓናል ውይይትና የኤግዚቢሽን መርሃ-ግብር ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026