የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ እየሠራች ነው-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Sep 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነገ የሚወሰነው ዛሬ በምንሠራው ሥራ ነው! የነገ ስኬታችን የሚቀረጸው በዛሬው ጥረታችን ነው። ከትናንት መልካም ልምዶችን በመቅሰም፣ ዛሬን በትክክል አጢኖ የነገን ራዕይ ዛሬ ላይ ሆኖ መገንባት የመንግሥታችን ጽኑ እምነትና መለያ ባህሪ ነው።

ሀገር በቀል ዕውቀትን ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር አስተሳስሮ ነገን ለመዋጀት መዘጋጀት ከዚህ ትውልድ የሚጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት እንደኾነ መንግሥት በፅኑ ያምናል፡፡ ለዚህም ነው ዲጂታላይዜሽንን እንደ አስቻይም እንደ ኢኮኖሚ ዘርፍም በመውሰድ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ያለው፡፡

ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳን እንጅ ዕዳን አታወርስም፡፡ ጊዜ በየአንጓዉ ለሚጠይቀዉ ጉዳይ ምላሽ መስጠት አለመቻል የትውልድ ዕዳ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሀገራችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ታዳጊዎችን በትምህርት ቤት እየመገበች የምታስተምረው፤ ለዚህም ነው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን በነፃ የኮደርስ ሥልጠና እያበቃች ያለችው፤ ለዚህም ነው የመጀመሪያውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ እያቋቋመች ያለችው ፡፡ ነገ ያለቴክኖሎጂ ዕውቀት፣ ነገ ያለሳይበር ደኅንነት፣ ነገ ያለመረጃ ሉዓላዊነት የሕልውና አደጋ አንደኾነ መንግሥታችን ይገነዘባል፤ ትውልዱን ለዚያ ያዘጋጃል፡፡

ለዘመናት ኋላቀር ሲባል የነበረዉ የኢኮኖሚ ዘርፍ ግብርና ነገ ያለቴክኖሎጂ ሕልውናዉ አደጋ ላይ ነው፡፡ ለተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ቅድመ ጥንቃቄ እና ምላሽ አሰጣጥ ዲጂታላይዜሽን ወሳኝ ነው፡፡ የመንግሥት አገልግሎቶችን በጥራት እና በፍጥነት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ያለፉት ዘመናት አሠራሮች አይደለም ነገ ዛሬም አዋጭ አይደሉም፡፡

በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እና ሥራ ፈጣሪ ወጣቶችን ለማፍራት ዲጂታል ክሕሎት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለእነዚህ ኹሉ ጉዳዮች ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ስለምትገኝ ነው “ኢትዮጵያ ነገዋን ዛሬ እየሠራች ነው” የምንለው፡፡

የጳጒሜን አምስተኛ ቀን የነገ ቀን ብለን ማክበራችንም መጪዉ ዘመን የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነትን የሚጠይቅ፣ መረጃ ትንተና ላይ የተመሠረተ ውሳኔ የሚሰጥበት፣ ከግብርና እስከ ሕዋ ሳይንስ ምርምሮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ የሚኾኑበት ዘመን ዋዜማ ላይ ስለምንገኝ ለዚያ የሚመጥን ትውልድ ለማፍራት እንደምንሠራ ለማስገንዘብ ነው፡፡

ጳጉምን 5 የነገ ቀን በሚል ስያሜ መከበሩ ዲጂታላይዜሽን ለነገዋ ኢትዮጵያ ግንባታ እና ሉዓላዊነት መከበር ሀገራችን ወደ ዲጂታላይዜሽን ሽግግር ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ለማብሰር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026