የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ ነው

Sep 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 8/2019 (ኢዜአ):- የሶማሌ ክልልን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች በብቃትና በጥራት እየተፈጸሙ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ።

አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።

አፈ ጉባዔው በዚሁ ወቅት፤ ለአቅመ ደካሞች የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ዜጎች የነበረባቸውን የቤት ችግር በመቅረፍ አስተማማኝ መጠለያ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ፌዴሬሽን ምክር ቤትም በክልሉ ከአቅመ ደካማ ወገኖች የቤቶች ግንባታ በተጨማሪ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማቅረብ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

እንዲሁም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አካባቢን በመጠበቅ ለቀጣይ ትውልድ የሚጠቅም መሠረት በመጣል የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።

የሶማሌ ክልል በመደመር መንግሥት የአስተዳደር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ፕሮጀክቶች እውን የሚሆኑበት ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

በዚህም የክልሉን ሕዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ የልማት ፕሮጀክቶች ተገንብተው የሕዝብን የልማት ጥያቄ በመመለስ ለአገልግሎት መብቃታቸውን አስረድተዋል።

ለአብነትም በማኅበራዊ ዘርፍ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የጤና ተቋማት ግንባታን በማስፋፋት ሕብረተሰቡ በአቅራቢያው የሕክምና አገልግሎት የሚያገኝበት ዕድል መፈጠሩን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በመንገድ፣ በአየር ማረፊያ መሠረተ ልማቶችና በኢንቨስትመንት ፍሰት የሕዝቡን ሁለንተናዊተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎች መመዝገባቸውን አብራርተዋል።

የመደመር መንግሥት የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ጀምሮ ማጠናቀቅ ዋነኛ መለያው መሆኑን በመጥቀስ፤ ይህም የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚነት እያሻሻለ መሆኑን አብራርተዋል።

የሶማሌ ክልል ሕዝብ ለዘላቂ ልማትና ሰላም ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ያሉት አፈ ጉባዔ አገኘሁ፤ በቀጣይም ቀጣይነት ያለው ሰላምና ልማት የማረጋገጥ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ከተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ሕብረ ብሔራዊነትን በማጠናከር በልማት ሥራዎች ያለውን ተሳትፎ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026

በክልሉ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል -ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ተኪ ምርቶችን የማምረት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ ...

Sep 3, 2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሥራ ዕድል ፈጠራ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት ተገኝቷል

ሆሳዕና፤ ነሀሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ዜጎችን በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገ...

Aug 12, 2026

በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦የመንግሥት በሙስናና ሕገ ወጥ ድርጊት የተሰማሩ አካላትን በሕግ ተጠያቂ የማድረግ ርምጃ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ኢዜአ...

Aug 12, 2026