🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መስከረም 26/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት ለዘላቂ ዕድገት መሠረት የሚሆኑ ወሳኝ የልማት ሥራዎችን እውን ማድረጉን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ትላንት ተካሒዷል።
በዚህም የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር ባለፉት ዓመታት በልማት፣ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ በዲፕሎማሲና መሰል ተግባራት ስኬታማ ስራዎች መመዝገባቸውን አብራርተዋል።
በተለይም ለትውልድ የሚተላለፉ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እውን በማድረግ በኢትዮጵያ ዘላቂነት ያለው እድገት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማስጠበቅና ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ላይ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል።
በቀጣይም በመደመር እሳቤ እነዚህንና መሰል የልማት ስራዎችን ይበልጥ በማጠናከር ለትውልዱ የተመቸች ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በእጅጉ ያሻሻሉ ናቸው።
በተጨማሪም የዜጎች እኩልነትና አካታችነት የተረጋገጠበት የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መፈጠሩን ገልጸው፤ ይህም ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ በባለቤትነት እንዲሳተፉ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወይዘሮ ሮማን ደመቀ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ አዳዲስና ፈጣን የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።
እነዚህ የልማት ስራዎች ለኢትዮጵያና ህዝቦቿ ትልቅ ተስፋን የሰነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በቀጣይ በመደመር መንግሥት የተጀመሩ ስራዎች በስኬት እንደሚጠናቀቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የዜጎች ተሳትፎ እንዲጠናከር ዕድል መፍጠር ችሏል ነው ያሉት።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ አበራ ሙላቱ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በሁሉም ዘርፎች ያከናወናቸው ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ይገልጻሉ።
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ሆኖ መጠናቀቁን በማሳያነት አንስተው፤ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ተስፋ ሰጪና የዜጎችን ጥያቄዎች የመለሱ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

የመደመር መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ በርካታ ተግባራትን በማከናወን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን የገለጸችው ደግሞ ወጣት መታሰቢያ ጠብቀው ናት።
የሌማት ትሩፋትና ሌሎች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች መከናወናቸውን ጠቅሳ፤ የልማት ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ዜጎች ከመንግስት ጋር በመተባበር ሊሰሩ ይገባል ነው ያለችው።

ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ተሾመ ቢያዝን በበኩላቸው፤ የመደመር መንግስት ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ምቹ ምህዳርን ለመፍጠር ያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሰሩ የኮሪደርና ሌሎች የልማት ስራዎች የሚያስደንቁ ብሎም የሀገሪቱን ፈጣን እድገት በተግባር ያሳዩና ለትውልድ የሚሻገሩ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026