🔇Unmute
አዳማ ፤ መስከረም 29/2019 (ኢዜአ) ፦ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የሰላምና የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል በንቃት እንሳተፋለን ሲሉ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
በዚህም ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሰየሙ ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ያስተላለፉትን መልዕክት መነሻ በማድረግ ኢዜአ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎችን አነጋግሯል።
ከነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ቃልኪዳን ወርቁ እንዳሉት ባለፉት አመታት በማህበራዊና በኢኮኖሚ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶች ህዝብን ተጠቃሚ አድርገዋል።

በአዲሱ የመደመር መንግስት ልማቶቹን ለማስቀጠል የቀረቡት ውጥኖች እንዲሳኩ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ተሷፏቸውን እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል።
ወጣት አብርሃም ሽመልስ በበኩሉ ባለፉት አመታት እንደሀገር ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ የሰላምና የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሷል።

አዲስ የተመሰረተው የመደመር መንግስት ውጤታማ የሰላምና የልማት ስራዎችን ለማስቀጠል ላስቀመጠው አቅጣጫ ስኬት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል።
አቶ ሶርቻ ቀቦንቻ በበኩላቸው፤ በመደመር መንግስት የተቀየሰው ስትራቴጂ እንደ ሀገር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታና እና የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።
የመደመር መንግስት የተጀመሩ ትላልቅ የልማት ስራዎች ለመፈጸምና ሰላምን ለማጽናት በሚደረገው ጥረት በንቃት እንደሚሳተፉም አስታውቀዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026