የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው

Oct 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቅ በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ርዕይ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

‎‎በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጋርነት የተቋቋመው ይህ ማጣሪያ ፋብሪካ፤ የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከር እና በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት ለመጨመር የተያዘውን ዓላማ ለማሳካት ትልቅ እመርታ ነው።

‎የማዕድን ዘርፍ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቅድሚያ የሚሰጠው አምራች ዘርፍ ሲሆን፤ በተለይም ወርቅ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። ይህ ተነሳሽነት የሀገሪቱን ሀብቶች ከሀገር ውስጥ ማቀነባበሪያ፣ ከኢንዱስትሪ አቅም እና ዘላቂ እሴት ፈጠራ ጋር ለማስተሳሰር የመደመር መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።


‎ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማጣራት አቅም ያለው ሲሆን፤ የወርቅ ጥራትን ለመለካት፣ ለማንጠር እና ለውጭ ገበያ ዝግጁ ወደሆኑ ንጹህ ወርቆች ለመቀየር፣ እንዲሁም በተለያዩ የጥራት ደረጃዎች የተሰናዱ የወርቅና የብር ጡቦች ለማምረት ታስቦ የተገነባ ነው።

‎ማጣሪያ ፋብሪካው በውድ ማዕድናት ማጣራትና ማምረት ረገድ ኢትዮጵያን የቀጣናው ማዕከል ለማድረግ መሠረት የሚጥል ሲሆን፤ የወርቅ ዋጋ አተማመን ላይ ግልጽነትን፣ የጥራት ማረጋገጫን እና እምነትን ያሳድጋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት ወደ ላቀ የሀገር ውስጥ እሴት፣ ጠንካራ የኢንዱስትሪ አቅም እንዲሁም በቀጣናዊ እና በዓለም አቀፍ ገበያዎች ሰፊ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚረዳ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው።


‎ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ግልጽ የሆነ ትልቅ ርዕይ ያነገበ ነው፤ ይህም ጥሬ ማዕድናትን ዝም ብሎ ከመቆፈር ባለፈ፣ ማቀነባበር፣ ማምረት እና በሀገር ውስጥ የላቀ እሴት መፍጠር ላይ የሚያተኩር ነው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026