🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በታይላንድ ባንኮክ እየተካሄደ የሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በዓመታዊው ስብስባ ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችንም እያካሄደ ነው።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ካሊድ መሐመድ ባላማ ጋር ተወያይተዋል።
የሁለቱ ሀገራት ማዕከላዊ ባንኮች ገዥዎች ውይይት በባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።
የሀገራቱን የፋይናንስ ሥርዓቶች ይበልጥ ለማቀራረብና ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026