የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የብሔራዊ ውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካው ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ሚና አለው 

Oct 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የብሔራዊ ውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መከፈት ሕገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ከመግታትና የኢኮኖሚ መዋቅሩን ከማሻሻል ባሻገር፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችንና የቴክኖሎጂ ሽግግርን እንደሚያመጣ የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) ገለጹ።

የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ከመሰረቱ ለማሻሻል በተገበረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትኩረት ከሰጣቸው ዘርፎች መካከል ማዕድን አንዱ ነው።


የማዕድን ዘርፉን በቴክኖሎጂ ታግዞ በማልማት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ እና ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በሳም ፕሬሺየስ ሜታልስ መካከል በተደረገ አጋርነት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ስራ መጀመሩ ይታወቃል።

‎ከማዕድን ማውጣት እስከ ኢንዱስትሪ ሽግግር ድረስ የላቀ እሴት እየተፈጠረ ሲሆን፤ ፋብሪካው በዓመት ከ600 ቶን በላይ ውድ ማዕድናትን የማንጠር አቅም አለው፡፡


የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ይህ ፋብሪካ በሀገር ውስጥ ምርት ላይ እሴት በመጨመር፣ የውጭ ንግድ ገቢን በማሳደግ እና የህገ-ወጥ ንግድ ዝውውርን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡፡

ፋብሪካው ሕገ-ወጥ የማዕድን ንግድ ዝውውርን ከመቆጣጠር አኳያ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑን ጠቅሰው፤ ፋብሪካው መቋቋሙ ከማዕድን ምንጭ ጀምሮ እስከ ውጭ ገበያ ድረስ ያለው አቅርቦት የቁጥጥር ሥርዓት እንዲጠናከር ያስችላል ብለዋል።

ፋብሪካው ፈቃድ ካላቸው ህጋዊ አቅራቢዎች ጋር ብቻ የሚሰራ በመሆኑ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን ህገ-ወጥ የማዕድን ንግድ ዝውውር በእጅጉ እንደሚቀንስም ነው የጠቆሙት፡፡

ወደ ውጭ የመላክ ሂደቶች በዲጂታል ሥርዓት መደገፉም የቁጥጥሩ ውጤታማነት የላቀ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

የውጭ ንግድና የንግድ ሚዛን ከማስተካከል አንጻር ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመው የተጣራና ጥራቱ የተጠበቀ ወርቅ እና ውድ ማዕድናት ወደ ውጭ መላክ ሲጀመር የሀገር ውስጥ የገቢ መጠን እያደገ እንደሚመጣም ነው የገለጹት፡፡


ኢትዮጵያ የምታቀርበው የምርት ዓይነት እየጨመረ በመሄዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነቷና የውጭ ንግድ አቅሟ እያደገ እንደሚሄድ ጠቁመው፤ በዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ለሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ኢንቨስትመንት ግብአት በመሆን አጠቃላይ የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን ያስተካክላል ብለዋል።

ከሥራ ዕድል ፈጠራና የቴክኖሎጂ ሽግግር አኳያም የፋብሪካው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው፤ ከማዕድን አውጪዎች ጀምሮ እስከ አቅርቦት፣ ማጣራት እና የጌጣጌጥ ኢንዱስትሪዎች ድረስ ባለው ሰንሰለት ውስጥ በርካታ ዜጎች የሚሳተፉበት ሰፊ የሥራ ዕድል ይፈጠራል ብለዋል።

ፋብሪካው መመሥረቱ አዲስ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስተዋወቅ በሌሎችም ዘርፎች ለሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታን እንሚፈጥርም ጠቁመዋል፡፡

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ማዕከል የሆነው የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ የሀገሪቱን የማዕድን ሀብት ከኢንዱስትሪ አቅም ጋር በማስተሳሰር የኢኮኖሚ መዋቅሩን ማጠናከር የሚያስችል ትልቅ ሀገራዊ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026