🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአፍሪካም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትልቅ አቅም እንዳላት የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የተቋሙ ልዑክ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝቷል።

በተጨማሪም ልዑኩ በጤናው ዘርፍ በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አብሮ መሥራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ከኢንስቲትዩቱ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት ኢትዮጵያ በኤአይ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በአፍሪካም እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ አቅም እንዳላት ተናግረዋል።
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) የጤና አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጁ የኤአይ መፍትሔዎችን አስተዋውቀዋል።
ሁሉም ዜጋ ከቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆን ሰፊ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የጤናውን ዘርፍ የሚለውጥበት፣ በአንደኛ ደረጃ የጤና ተቋማት ውስጥ ሥራ ላይ የሚውልበት እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ልዑካኑ ኢንስቲትዩቱ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር (NLP) ያከናወናቸው ሥራዎች አስደናቂ መሆናቸውን በመግለጽ፣ የማሽን ቋንቋ እና የንግግር ማወቂያ ቴክኖሎጂዎች ለጤናው ዘርፍ ሰፊ ጠቀሜታ እንዳላቸው አንስተዋል።
እንደ ኤአይ ያሉ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በአህጉሪቱ መስፋት እንዳለባቸው ጠቅሰው ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመሥራትና አጋርነትን ለማጠናከር ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026