🔇Unmute
መቱ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በዘንድሮው ዓመት 500 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ ሩዝ እንደሚለማ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) አስታወቁ።
በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) የተመራ የስራ ሃላፊዎች ቡድን በመቱ ከተማ የሚገኘውን የሩዝ መፈልፈያ ፋብሪካን ጨምሮ በአጎራባች ወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ዋና አስተዳዳሪው በዚሁ ወቅት፤ በዞኑ በተለይም በተለያዩ የግብርና መስኮች በስፋት ያልተሰራባቸው እምቅ አቅሞችና ምቹ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል።

የሩዝ ልማት ከእነዚህ አቅሞች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ረሻድ፤ በ2019 ዓ.ም በዞኑ 500 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የሩዝ ልማት ለማከናወን ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።
ከሚታረሰው ሔክታር መሬትም 23 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት የሚሰራ መሆኑን ነው ያነሱት።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሩዝ መፈልፈያ ፋብሪካ ግንባታ ላይ ተሰማርተው ወደስራ የገቡትን ባለሀብቶች ጨምሮ ሌሎችን በመደገፍ ወደስራው እንዲገቡ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት የሚጠናከር መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዞኑ የቡና ፣ ሻይ፣ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ኢኒሼቲቭ አቅሞችንም ይበልጥ በማጠናከር የአርሶ አደሩን ገቢና አጠቃላይ የሀገርን ዕድገት ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎች በቁርጠኝነት ይከናወናሉ ብለዋል።
በመቱ ከተማ የተገነባው 'ናፊካ' የሩዝ መፈልፈያ ፋብሪካ ተወካይ ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኮማንደር ሙላቱ ቡልቻ፤ ፋብሪካው በአሁኑ ወቅት በቀን እስከ 500 ኩንታል ሩዝ የሚፈለፍል መሆኑን ተናግረዋል።

ቀደም ሲል አርሶ አደሮች የሩዝ ምርታቸውን ወደሌላ ቦታ ይልኩ እንደነበር አንስተው አሁን ግን ይህ ፋብሪካ ተጠቃሚነታቸውን እንደሚያሳድገው ተናግረዋል።
ፋብሪካው አሁን ላይ 50 ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረ መሆኑን በማንሳት ወደፊት እስከ 250 ለሚደርሱ ሰዎች የስራ እድል የመፍጠር አቅም እንዳለውም ነው የገለጹት።
አቶ ፍሬው ሽጉጥ በፋብሪካው የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ሰዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ ከስራው በሚያገኙት ገቢ ሕይወታቸውን እየመሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከስራው የሚያገኙት ልምድና እውቀትም ወደፊት የራሳቸውን ስራ ለመፍጠር እንደሚያግዛቸው አንስተዋል።
በሌላ በኩል የስራ ሃላፊዎቹ የመቱ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ጨምሮ የመቱ ጎሬ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታና ሌሎች ስራዎችንም ተመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026