የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሸገር ከተማ ለግብርና ምርታማነት ያሉ ዕድሎችን በመጠቀም በተሰራው ስራ ውጤት እየተገኘ ነው

Oct 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሸገር ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ከተማ ለግብርና ምርታማነት ያሉትን ዕድሎችና አቅሞች በመጠቀም በተሰራው ስራ ውጤት እየተገኘ መሆኑንየሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሪድ ድምሩ ገለጹ።

በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገላን አራብሳ ወረዳ በኩታገጠም ምርጥ ዘር የስንዴ ልማት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሁሉን አቀፍ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከለወጡ ዓመታት ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን በስትራቴጂ በመመራት እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ዘላቂና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ በመገንባት በየደረጃው የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

በተለይም ባለፉት የለወጥ ዓመታት በግብርናው ዘርፍ በተከናወኑ ስራዎች ዘርፉን ከዘልማዳዊ እንቅስቃሴ ወደ ፈጣን እድገት በማሸጋገር ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል።


ይህም የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና የሀገሪቱን የውጭ ላኪነት አቅም ወደ ከፍተኛ ደረጃ የማሸጋገር ግቦችን በማሳካት ላይ ይገኛል።

በሸገር ከተማም ለግብርና ምርታማነት ያሉትን ዕድሎችና አቅሞችን በመጠቀም የተያዙትን ግቦች ለማሳካት ቴክኖሎጂን በማስፋፋት በተሰራው ስራ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚገኘው ውጤት እየጨመረ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ገላን አራብሳ ወረዳ በክረምት ዝናብ የለማ የኩታገጠም ምርጥ ዘር የስንዴ ልማት በዛሬው እለት የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባና የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሪድ ድምሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ዘመናዊ ግብርና፡ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ራስን የመቻል ጉዞን እውን ያደርጋል።

በተለይም የስንዴ ምርታማነት በአጭር ጊዜ ውስጥ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና ከአቅርቦት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።


በሸገር ከተማም እነዚህን ግቦች ለማሳካት ያሉትን አቅሞች ወደ ስራ በመቀየር በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት።

መርሐ ግብሩ በግብርናው ዘርፍ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት ያለመ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የሸገር ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበራ ጫላ ናቸው።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በተለይም ምርታማነትን ለማሳደግና የተገኙ ስኬቶችን ለማስፋፋት መሆኑን አንስተዋል።

በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ለሚ ረጋሳ በበኩላቸው፤ ዘመናዊ ግብርና የኢኮኖሚ ሽግግር መሠረት መሆኑን ገልጸው፣ በዚህ ረገድ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስፋፋት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026