የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አርሶአደሮች በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ውጤታማ ሆነዋል

Oct 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ፣ ጥቅምት15/2019 (ኢዜአ)፡-የጅማ ዩኒቨርሲቲ ባደረገላቸው ዘመናዊ የንብ ቀፎ አቅርቦትና የሙያ ድጋፍ በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ውጤታማ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ።

ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በተለይም የዴዶ ወረዳ ለአበቦችና ለተፈጥሮ ዕፅዋት የተመቸ የአየር ጠባይ ያለው በመሆኑ ለንብ ማነብ ሥራ ከፍተኛ ተፈጥሮአዊ አቅም ያለው አካባቢ ነው።

ሆኖም ከአሁን ቀደም በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች አብዛኛውን የንብ ማነብ ሥራ የሚያከናውኑት በባህላዊ ቀፎዎችና በዛፎች ላይ በሚሰቀሉ ባህላዊ አሰራሮች በመሆኑ፣ የሚገኘው የማር ምርት መጠን አነስተኛ፣ ጥራቱ ዝቅተኛና የንቦችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነበር።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመማር-ማስተማርና ከምርምር ሥራ ጎን ለጎን፣ የምርምር ውጤቶችንና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በቀጥታ ወደ አካባቢው አርሶ አደሮች በማውረድ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በስፋት ይሰራል።

የዴዶ ወረዳ አርሶ አደሮች ዩኒቨርሲቲው ባደረገላቸው የዘመናዊ ንብ ቀፎ አቅርቦትና የሙያ ስልጠና ድጋፍ በንብ ማነብ ሥራ ተሰማርተው ሥራውን በጀመሩ በዓመታቸው ያመረቱትን ጥራት ያለው የማር ምርት ለገበያ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በወረዳው ኦፎሌ ቀበሌ የንብ ማነብ ሥራ ከተሰማሩት አርሶ አደሮች መካከል፣ ዩኒቨርሲቲው ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን በማቅረብና የሙያ ድጋፍ በማድረግ የማር ምርት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ እያገዛቸው መሆኑን ተናግረዋል።

አርሶ አደር ይስሐቅ አየለ እንደተናገሩት፣ በንብ ማነብ ሥራ መሰማራታቸው ለወደፊት የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለመፍጠር ተስፋ ሰጥቷቸዋል።

ከሌሎች ሦስት አርሶ አደሮች ጋር በመደራጀት በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ዘመናዊ ቀፎ ማግኘታቸውን የገለጹት አርሶ አደሩ፤ በተደረገላቸው የሙያ ድጋፍ ሥራውን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን እንደቻሉም አስረድተዋል።


ሌላኛው አርሶ አደር መሐመድ አባዲጋ በበኩላቸው፣ ወደ ንብ ማነብ ሥራው ከመግባታቸው አንድ ዓመት በፊት በዩኒቨርሲቲው መምህራን የሙያ ሥልጠና እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

ከሥልጠናው በኋላ ባገኙት ዘመናዊ ቀፎ ድጋፍ ሥራውን መጀመራቸውን ጠቅሰው፣ በአሁኑ ወቅት ያመረቱትን ማር ለገበያ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በተመሳሳይ ወይዘሮ አለዊያ ከድር፣ ዩኒቨርሲቲው ሴቶችን በማደራጀት ዘመናዊ ቀፎዎችንና የሙያ ድጋፍ በማቅረብ ወደ ምርታማ ሥራ እንዲሰማሩ እያገዛቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም አብዛኛውን ጊዜ ያለ ሥራ በቤት ውስጥ እንደሚያሳልፉ የገለጹት ወይዘሮ አለዊያ፣ በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ወደ ንብ ማነብ ሥራ በመግባት በትጋት እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና እንስሳት ሕክምና ኮሌጅ መምህርና የፕሮግራሙ አስተባባሪ ዋሲሁን ሀሰን (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች አርሶ አደሮችን በማደራጀትና የሙያ ድጋፍ በማድረግ ከግብርና ሥራዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል።


ዩኒቨርሲቲው በቡና ልማት፣ በእንስሳት እርባታና በሌሎች የግብርና ዘርፎች ለአርሶ አደሮች፣ ለሴቶችና ለወጣቶች ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም ከ70 በላይ ሴቶችን በማደራጀት በዶሮ እርባታ ሥራ እንዲሰማሩና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ጠቅሰው፣ በዘንድሮው ዓመትም ዘመናዊ የንብ ቀፎዎችን በማቅረብ አርሶ አደሮች ከሥራው ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በቴክኖሎጂ የተደገፉ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን በማዘጋጀት ከ500 በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ተደራሽ የማድረግ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ ዶክተር ዋሲሁን ጠቁመዋል።

በቀጣይም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በርካታ አርሶ አደሮችን፣ ሴቶችንና ወጣቶችን ከተለያዩ የግብርና ሥራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ መሆኑንም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026