🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የግብርናና የምግብ ሥርዓትን መለወጥ የሚያስችሉ በርካታ የልማት መርሃ ግብሮችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት እያስገኘች መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ገለጹ።
የአፍሪካ ሳይንስና ኢኖቬሽን ፎረም 2026 በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) ጨምሮ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ የአነስተኛ አርሶ አደሮች ተወካዮች፣ ወጣቶች እና የልማት አጋሮች ታድመዋል።
ፎረሙ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂንና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው።
በተጨማሪም ፎረሙ ምርታማነትን በመጨመር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ እና የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ነው።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሳይንስና ፈጠራን የአርሶ አደሮች፣ የአርብቶ አደሮች፣ የምግብ አቀነባባሪዎች፣ የነጋዴዎች እና የተጠቃሚዎችን ኑሮ የበለጠ ማሻሻል የሚያስችል ማድረግ ይገባል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የግብርናና የምግብ ሥርዓትን መለወጥ የሚያስችሉ ውጤታማ ኢኒሼቲቮችን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤቶች እያስገኘች መሆኑን ገልጸዋል።

የአረንጓዴ ዐሻራ፣ የሌማት ትሩፋትና ሌሎች የልማት መርሃ ግብሮች ለዚህ ለውጥ ወሳኝ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በዘርፉ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ምርታማነትን ማሳደግ፣ የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ማስፋፋት እንደሚገባም አመላክተዋል።
በተለይም በገጠር ለሚኖሩ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅርቦትን ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሳይንስና ፈጠራ ለዚህ ለውጥ አንቀሳቃሽ ሞተር መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የምታደርገውን ኢንቨስትመንት እያሳደገች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
በግብርና ሥርዓታችን የሚከሰቱ አደጋዎችን አስቀድሞ የመገመት፣ የሚያስከትሉትን ተጽዕኖ ለመቋቋም የመዘጋጀትና ኪሳራን ለመቀነስ በቂ እርምጃ የመውሰድ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዚህም የአፍሪካ ሀገራት የተሞክሮ ልውውጥንም ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመው፤ ኢትዮጵያ ተሞክሮዋን ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

የዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ተወካይ ዶክተር አበበ ሀይለገብርኤል በበኩላቸው፤ ግልጽ ኃላፊነት እና የጊዜ ሰሌዳ የሌለው ቃል ኪዳን ባዶ ተስፋ ሆኖ የመቅረት ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ለዘርፉ ተጨማሪ ወጪዎችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፤ ለወጣው ወጪ ተመጣጣኝ እሴት መገኘቱን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
እንዲሁም አምራቾች እና ተጠቃሚዎች ትርጉም ያለው መሻሻል ማየታቸውን መጠየቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ዋና ጸሃፊ እና ዋና ኢኮኖሚስት ሀናን ሞርሲ(ዶ/ር) ፤ ከሞዴል ፕሮጀክቶች ወደ ሰፊ ትግበራ መሸጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል።
መንግሥታት፣ የምርምር ተቋማት፣ አርሶ አደሮች፣ ባለሀብቶች እና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እንደ አንድ የተቀናጀ የፈጠራ ሥነ-ምህዳር ሆነው መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ፎረሙ ሳይንስና ፈጠራ በአፍሪካ የግብርናና ምግብ ሥርዓት ሽግግር ውስጥ ማዕከል መሆን አለባቸው የሚለውን የጋራ እምነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) የአፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ተወካይ አይመን ኦማር ናቸው።
የፎረሙ ዓላማ ሳይንስን ከፖሊሲ፣ ፈጠራን ከኢንቨስትመንት፣ እንዲሁም እውቀትን ከተግባር ጋር ማገናኘት መሆኑን አመልክተዋል።
ፎረሙ ሳይንስን፣ ቴክኖሎጂንና ኢኖቬሽንን በመጠቀም በአፍሪካ የምግብና ግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ አህጉራዊ መድረክ ነው።
በተጨማሪም ምርታማነትን በማሳደግ፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ የግልና የመንግሥት ኢንቨስትመንቶችን በማሳደግ አህጉራዊ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ላይ ያተኮረ ፎረም ነው።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026