🔇Unmute
ሳጃ ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መሰተዳድር የትምጌታ አስራት(ዶ/ር) አስታወቁ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶች ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ከየም ዞን ነዋሪዎች ጋር በሳጃ ከተማ መክረዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።
የየም ዞን እምቅ የተፈጥሮ ጸጋዎች ከሚገኙባቸው አካባቢዎች አንዱ መሆኑን ጠቁመው ዞኑ በተለይ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ላይ ለሌሎች አብነት የሚሆን ላቅ ያለ ሀገር በቀል እውቀት ያለው ነው ብለዋል።
የም ተፈጥሮን የመንከባከብና ወደ ልማት የመቀየር የካበተ ልምድ ያለው ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ልምዱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል።
የክልሉ መንግሥት በቀጣይ ለማከናወን ያቀዳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በየደረጃው የሚነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመፍታት በሚደረግ ጥረት ህዝቡ አበርክቶውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የም የትብብር፣ የአብሮነት እና የአንድነት እሴቶች ባለቤት መሆኑን ተናግረዋል።
እሴቶቹን መሰረት በማድረግ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይሁን አሰፋ በበኩላቸው፤ በዞኑ የተፈጥሮ ሀብቶችን ለልማት በማዋል የህዝብ ተጠቃሚነትን የበለጠ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የመንገድ፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች የመሰረት ልማት ተቋማትን የማስፋፋት ስራም እንደሚከናወን አመልክተዋል።
ከምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ አባቢያ አባገላን፤ በመንግስት የተያዙ እቅዶች ሰላምን በዘላቂነት በማረጋገጥና ልማትን አጠናክሮ በማስቀጠል ህዝብን ይበልጥ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።
ለእቅዱ ተግባራዊነት የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ተሳታፊ ወይዘሮ አሚና አደም የተያዙ የልማት እና የሰላም እቅዶች በተለይም ሴቶችን ማዕከል ያደረጉ በመሆናቸው ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
እቅዶቹን ለማሳካት ከመንግሥት ጎን በመቆም የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በዞኑ መንገድ፣ ውሃ፣ መብራትና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን ለማስፋፋት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ለህዝቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ መሆናቸውን የተናገሩት ደግሞ አቶ ግዛቸው ጋሼ ናቸው።
በምክክር መድረኩ ላይ የክልልና የየም ዞን አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026