የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

በሰሜን ሸዋ ዞን የደረሱ ሰብሎችን ካልተጠበቀ ዝናብ ለመታደግ ርብርብ እየተደረገ ነው

Oct 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ብርሃን፣ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፡- በሰሜን ሸዋ ዞን የደረሱ ሰብሎችን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለመከላከል ዘመናዊ የምርት መሰብሰቢያ ማሽኖችንና ባህላዊውን የደቦ አሰራር በመጠቀም ፈጥኖ የመሰብሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያ ወይዘሮ ሁሉም ታየ ዘነበ ለኢዜአ እንደገለጹት ለያዝነው የመኸር ምርት ዘመን በዞኑ 563ሺህ 282 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል።

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በግብርና ባለሙያዎች በመታገዝ አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ፈጥኖ እንዲሰበስብ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።

እስካሁን በተደረገው ጥረትም በ75ሺህ 525 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ የደረሰ ሰብልን በዘመናዊ የምርት መሰብሰቢያ ማሽኖችና ደቦን በመጠቀም መሰብሰብ መቻሉን አስረድተዋል።

በቀጣይም አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብላቸውን ፈጥነው በመሰብሰብ ወደ ጎተራ በማስገባት የምርት ብክነትን ለመቀነስ በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ መውረዱን ተናግረዋል።

በዞኑ በያዝነው የመኸር ምርት ዘመን 20 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026