የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች ቡናን በጥራት በማዘጋጀት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ ነው

Oct 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዲላ፤ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ)፡-የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች ቡናን በጥራት በማዘጋጀት ለውጭ ገበያ ለማቅረብና የተሻለ ዋጋ ለማግኘት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወኑ መሆናቸውን ገለጹ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ46 ሺህ 800 ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ ምርትን በጥራትና በጥንቃቄ ሰብስቦ የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ መሆኑም ተመላክቷል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የጌዴኦ ዞን አርሶ አደሮች የደረሰ የቡና ምርትን በጥራትና በጥንቃቄ ሰብስበው በማዘጋጀት የተሻለ ገበያ ለማግኘት እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በዞኑ ወናጎ ወረዳ የሚኖሩት አርሶ አደር አስቴር ሽፈራው እንዳሉት ለቡና ተክላቸው አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በተለይ ያረጁትን በማንሳት በተሻሻለ ዝሪያ የመተካት ሥራ ማከናወናቸው የቡና ምርትና ጥራት እንዲሻሻል ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም የደረሰውን ምርት በመሰብሰብ ልዩ ጣዕም ቡና በጥራት እያዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በገበያው የተሻለ ዋጋ ለማግኘት እንደሚያስላቸው ተናግረዋል።

ከ160 ኩንታል በላይ ልዩ ጣዕም ቡና በጥራት በማዘጋጀት የተሻለ ዋጋ ለማግኝት እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ሌላኛው አርሶ አደር ባሊ ሞኬ ናቸው።


መንግሥት ለቡና ልማት የሰጠው ልዩ ትኩረትና ድጋፍ በቡና ምርታማነት፣ በጥራትና በገበያ ትስስር ውጤት በማምጣት ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ገልጸዋል።

አርሶ አደር ወልደማርያም አራርሶ በበኩላቸው የቡና ልማት ለብዙዎች የገቢ ምንጭና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ከመዋል ባለፈ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት አበርክቶው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል።


የግብርና ባለሙያዎችን ምክረ ሃሳብ ተከትለው የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በዘመናዊ መንገድ በማልማታቸው ማርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ቡናን በጥራት በማዘጋጀት በቀጥታ ትስስር ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

በጌዴኦ ዞን ኩታ ገጠም የቡና ልማት ዘመናዊ አሰራርን በማጠናከር የቡና ምርትና ጥራትን ማሳደጉን የገለጹት ደግሞ የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ ሩፎ ናቸው።


ጥራት ላለው ቡና የተሻለ ዋጋ የሚከፈልበት ሥርዓት መዘርጋቱ የቡና ጥራትና አቅርቦትን እያሻሻለ መሆኑንም ተናግረዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ ቸካ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ውጤታማ የቡና ልማት ሥራዎች ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል።

በበጀት ዓመቱም ከ46 ሺህ 800 ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህም ምርትን በጥንቃቄ የመሰብሰብና በጥራት የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይ የቀጥታ ትስስር ተጠቃሚ አርሶ አደሮች የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ልዩ ጣዕም ቡና እንዲያዘጋጁ ድጋፍና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026