የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ትብብር የተሳሰሩ ናቸው - ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

Oct 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሞስኮ፤ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ሩሲያ በረጅም ዘመናት ውስጥ በተገነባ ተምሳሌታዊ ትብብር የተሳሰሩ ሀገራት መሆናቸውን የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በ3ኛው የአፍሪካ - ሩሲያ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ሞስኮ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋርም በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።


ኢዜአ ከስፍራው እንደዘገበው በውይይቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ከኢኮኖሚያዊ ትስስር ባሻገር በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ቅርበት አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህ የጋራ የሞራል እሴት በብዙ ደረጃ ሕዝቦችን የሚያቀራርብ አስፈላጊ መሠረት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስረድተው ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ የልማት መስኮች በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ የገለጹት ፑቲን፣ በተመድ፣ በብሪክስ እና በሌሎችም ባለብዙ ወገን መድረኮች ውይይቶች መደረጋቸውን አንስተዋል።

አፍሪካ በከፍተኛ የእድገት ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ትብብር የአህጉሪቱን ተስፋ ሰጪ እድገት በጋራ ለማስቀጠል ማሳያ ነው ብለዋል።

የአፍሪካ ሀገራት ሁለንተናዊ ብልፅግና ሊሳካ የሚችለውም ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ ጭምር መሆኑን ገልጸው፣ በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅ የወደፊት እድገት ዋና መሠረት ከሚሆኑ ተስፋ ሰጪ ዘርፎች አንዱ ነው ብለውታል።


እንደሳቸው ገለጻ ዘርፉ እንዲያድግ የሂሳብና የሳይንስ ትምህርት ቤቶች፣ ማዕከላት ፣የሰው ኃይል እና የኃይል አቅርቦት መሠረተ ልማቶች ወሳኝ ናቸው።

ሩሲያ በእነዚህ መስኮች ያላትን ዕምቅ አቅም ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ለማጋራት ዝግጁ መሆኗንም አክለዋል።

ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ከቀድሞ ሶቪየት ሕብረት ጀምሮ የአፍሪካ ሀገራትን የነፃነት ትግል በመደገፍ የተገነባ ታሪካዊ የትብብር መሠረት እንዳላት ጠቅሰዋል።

አሁን ግን የሩሲያ እና የአፍሪካ ትብብር ወደፊት በማተኮር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ሊያፋጥን ወደሚችል ምዕራፍ መሸጋገር እንዳለበትም አመልክተዋል።

የ3ኛውን የሩሲያ - አፍሪካ ጉባዔ ውይይቶችን ተከትሎ ማጠቃለያ መግለጫዎች የሚጠበቁ ሲሆን ከ2027 እስከ 2029 የሚዘልቀው አዲስ የሩሲያ እና የአፍሪካ አጋርነት የትግበራ ዕቅድ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026