🔇Unmute
ጊምቢ፣ ጥቅምት 19/2019 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በቡና ምርት እየተገኘ ያለውን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እና ስኬት በሻይ ልማትም ለመድገም አበረታች ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸው ተገለጸ።
የጉሊሶ ወረዳ ምክትል ሃላፊና የግብርናና መሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ታደሰ እንደገለጹት፤ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የሻይ ልማትን በአርሶ አደር ደረጃ በስፋት ለማልማት ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።

አሁን ላይ ወረዳው ትኩረት ከሰጣቸው የልማት ኢኒሼቲቮች መካከል የሻይ ልማት ግንባር ቀደም መሆኑን አመልክተው፤ በተለይም በዘንድሮው የምርት ዓመት ወደ 600 ሺህ የሻይ ችግኝ መዘጋጀቱንና በስፋት እንዲለማ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ተናግረዋል።
ዕቅዱን ውጤታማ ለማድረግም ግልጽ የትኩረት አቅጣጫዎች ተይዘው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።
የሻይ ልማት አርሶ አደሩ ከዚህ ቀደም በቡና ምርት ላይ ብቻ ተወስኖ የቆየውን የገቢ ምንጭ በማብዛት ሁለገብ ተጠቃሚ እንዲሆን ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ሃላፊው ገልጸዋል።
የሻይ ልማት ለአርሶ አደሩ የኑሮ ማሻሻያ እና ለቀጣይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም አክለዋል።
ይህ የልማት ጅምር በጉሊሶ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከቡና ልማት ጎን ለጎን በሻይ ልማትም በመሳተፍ የኢኮኖሚ አቅማቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ሰፊ ዕድል የሚፈጥር መልካም ዜና መሆኑንም አቶ መንግሥቱ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...
Sep 4, 2026