የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የምንገነባት አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ የምንገነባት አዲስ አበባ ነዋሪዎቿን በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደርን ለአካባቢው የልማት ተነሺዎች አስረክበናል ብለዋል።


የከተማ ልማት ዋነኛ ዓላማ መሠረተ ልማትን መገንባት ብቻ ሳይሆን የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል፣ መብትና ጥቅም ማስጠበቅ እና የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠር ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ እየተገነባ የሚገኘው የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የሀገራችንን የቴክኖሎጂና የኢኮኖሚ እድገት የሚያፋጥን ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ነው።ሆኖም ፕሮጀክቱ ቀደም ሲል መሬቱን ለእርሻ፣ ለግጦሽና ለመኖሪያነት ሲጠቀሙ የነበሩ አርሶ አደሮችን ሕይወት የሚነካ በመሆኑ፣ የልማቱ ተጠቃሚ እንጂ ተጎጂ እንዳይሆኑ ልዩ ትኩረት ሰጥተናል ብለዋል።

በዚህም መሠረት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ የልማት ከእርሻና መኖሪያ ቦታቸው ተነሺ ለሆኑ የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ አርሶ አደሮች የተቀናጀ መኖሪያ መንደር ገንብተን፣ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉ አቅርቦቶችንም አካተናል ነው ያሉት።


ይህም የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር ጠብቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ሁኔታ የሚያሸጋግር ሰው ተኮር የልማት አሠራር ነው ብለዋል።

ከመኖሪያ ቤቶች በተጨማሪ መንደሩ የሚከተሉትን አቅርቦቶች ይዟል፦

የወተት ላሞችን የሚይዙ የከብት ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ።

የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች።

የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል።

የስብሰባ አዳራሽ።

እነዚህ አቅርቦቶች ነዋሪዎቹ የተሻለ መኖሪያ እንዲኖራቸው፣ የወተት ልማትና ሌሎች የገቢ ምንጮቻቸውን እንዲያሳድጉ፣ ማኅበራዊ ትስስራቸውን እንዲጠብቁ እና ልጆቻቸው ምቹ አካባቢ እንዲያገኙ የተዘጋጁ ናቸው ብለዋል።

ልማት ማለት ሰውን ከነበረበት ቦታ ማንሳት ብቻ ሳይሆን የኑሮ ደረጃውን ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር መሆኑንም ገልጸዋል።


የአካባቢው ነዋሪዎች ቦታው ለታላቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንደሚውል ስናስረዳቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ለልጆቻቸው የመማር ዕድልና ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም እንደሚፈጥር በመገንዘብ በፈቃደኝነት ትብብራቸውን አድርገዋል ብለዋል።

ለዚህ ከልብ እናመሰግናለን፤ ትልቅ ክብርም ይገባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።

ይህ ተግባር በመደመርና በትብብር ስንሰራ ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ ማድረግና ዘላቂ ልማትን ማረጋገጥ እንደምንችል ማሳያ ነው።


የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ ነዋሪዎች መንደር ይህንኑ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫችንን በተግባር የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብለዋል።

የምንገነባት አዲስ አበባ የሁሉም ነዋሪዎቿን ክብር፣ መብትና ጥቅም የምታስጠብቅ፣ ሁሉንም በእኩል የልማት ተጠቃሚ የምታደርግ ከተማ እንድትሆን ቁርጠኛ ነን ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026