የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

አዲስ አበባ፤ በዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት መድረኮች ተከታታይ እውቅና እያገኘች ያለች ከተማ

Nov 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ከተማን መለወጥ የሚቻለው በግልጽ ራዕይ፣ በተቀናጀ ጥረትና የሰው ልጅን ሕይወት ማዕከል ባደረገ የልማት አቅጣጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ አዲስ አበባም ይህንን እሳቤ በተግባር እየተረጎመች መሆኗን በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም አስመስክራለች ብለዋል።

በቅርቡ በቻይና ሻንሃይ ከተማ በተካሄደው የ2026 የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማት ውድድር፣ አዲስ አበባን ጨምሮ አምስት ከተሞች ተሸላሚ ሆነዋል ነው ያሉት።

በዘንድሮው የሻንሃይ ሽልማት እውቅና ያገኙት፦


1. አዲስ አበባ (ኢትዮጵያ)


2. ሳንቲያጎ ዴ ካሊ (ኮሎምቢያ)


3. ኢስታንቡል (ቱርኪዬ)


4. ጂንግዴዠን (ቻይና)


5. ካቶቪስ (ፖላንድ) መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለአራተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ በአራቱ ዙሮች ሁለት ጊዜ እውቅና አግኝታለች በማለት አስታውሰዋል።

በ2024 የሴኡል ስማርት ሲቲ ሽልማትን፣ በ2026 ደግሞ የሻንሃይ ዓለም አቀፍ የዘላቂ ከተማ ልማት ሽልማትን አግኝታለች ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ በ2023 አዲስ አበባ በምገባ ፕሮግራምና በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዘርፎች ፈጣን ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ከተማ በመሆኗ ዓለም አቀፍ እውቅናና ሽልማት ማግኘቷን ጠቁመዋል።

ይህ እውቅና ለሀገራችን ታላቅ ክብር ከመሆኑም በላይ፣ እየሠራን ላለነው ሥራ ብርታትና ተጨማሪ ተነሳሽነት የሚሰጥ ነው ሲሉም አክለዋል።

ከሁሉም በላይ፣ በከተማችን የምንተገብራቸው ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃና የአኗኗር ሁኔታ ለማሻሻል የምናደርገው ጥረት፣ እንዲሁም የከተማዋን የተፈጥሮና ማኅበራዊ ፀጋዎች ወደ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የመቀየር ሥራችን ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን የሚያረጋግጥ ዓለም አቀፍ ምስክርነት ነው።

የመደመር እሳቤያችንም ልማትን ከሰው ሕይወትና ደኅንነት ጋር አጣምሮ ያያል። ከተሞች የሥልጣኔ መገለጫ እንዲሆኑ፣ ያላቸውን ፀጋዎች በመለየትና በማልማት፣ የሰውን አቅም ከተፈጥሮና ከኢኮኖሚያዊ ሀብቶች ጋር በማቀናጀት ለጋራ ብልፅግና መሥራትን ይጠይቃል።

በከተማችን የልማት ጉዞ እስካሁን የተጓዝነው ርቀት ጠንካራ መሠረት የጣለ ቢሆንም፣ የሚቀረን ረጅም ጉዞ እንዳለ እናውቃለን።

ሀገራችን ኢትዮጵያም ለዘመናት ከተጫኗት ድህነትና ልዩ ልዩ ችግሮች በዘላቂነት ለመላቀቅ፣ ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣትና ወደ ብልፅግና ለመሸጋገር የጀመረችው ጉዞ ፍሬ እያፈራ ይገኛል።

ሆኖም ይህንን እልህ አስጨራሽ ጉዞ ወደ ተሟላና ዘላቂ ለውጥ ለመቀየር የሁሉንም ዜጎች ርብርብ፣ ቁርጠኝነትና ተሳትፎ ያስፈልጋል።


ስለሆነም ሁላችንም ለለውጡ በቁርጠኝነት መትጋት ይገባናል ብለዋል።

ያገኘነውን ዓለም አቀፍ እውቅናም እንደ መዳረሻ ሳይሆን፣ እንደ ተጨማሪ ኃላፊነትና ለበለጠ ሥራ ማበረታቻ እንወስደዋለን ሲሉም አክለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ አያይዘውም፣ ይህንን ተነሳሽነት በመያዝ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች የሥልጣኔና የብልፅግና መሠረት እንዲሆኑ እንሠራለን ብለዋል።

አቅሞቻችንን በመደመር፣ ፀጋዎቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በመቀየር፣ ክብራችንን የሚመጥን የብልፅግና ግብ ለመድረስ ትጋታችንን እናጠናክራለን በማለትም ገልጸዋል።

ከተሞቻችን የመደመር ሥልጣኔ መዳረሻ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹና ተስማሚ የኑሮ አካባቢ፣ ለቀጣዩ ትውልድም ዘላቂ የብልፅግና ውርስ እንዲሆኑ በጋራ እንሠራለን ሲሉም አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026