የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ህይወት እና ጉዞ

የተቀናጀ መሠረተ ልማት በአፍሪካውያን መዲና- አዲስ አበባ

Nov 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ በከተማ ልማት የጀመረችው ጉዞ የአንድን ከተማ ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የከተማ ልማት ምን ያህል የዜጎችን ሕይወት መለወጥ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ማፋጠን እና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለ ከተማ መገንባት እንደሚችል የሚያሳይ ተግባራዊ ምሳሌ ሆኗል።

በተቋማዊ አቅም ግንባታ፣ በተቀናጀ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመን፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በከተማ አስተዳደር ብቃት ረገድ የተከናወኑ ሥራዎች ከተማዋን ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ አሸጋግረዋል።


የመንገድ፣ የውሃ፣ የፍሳሽ፣ የመብራት፣ የትራንስፖርትና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በተቀናጀ መልኩ ማስፋፋት የከተማዋን ተደራሽነት፣ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የአገልግሎት ጥራት እያሳደጉ ነው።

በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ልማት ረገድ የተከናወኑ ሥራዎችም የከተማዋን ውበት ከማሻሻል ባለፈ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መላመድና ተፅዕኖውን መቀነስ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው።

በዚህም አዲስ አበባ በአለምአቀፍ ደረጃ እውቅናዎችን በተከታታይ አመታት በተለያዩ ዘርፎች እንድታገኝ አድርገዋታል።

በተለይም የተበከሉ ወንዞችን በማጽዳት፣ የወንዝ ዳርቻዎችን በማልማትና ወደ መዝናኛ፣ መስተንግዶና የቱሪዝም ማዕከላት በመቀየር ከተማዋ ከተፈጥሮ ጋር ያላትን ግንኙነት እያደሰች ትገኛለች።

ከዚህም በላይ የመዝናኛ ስፍራዎችን፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን፣ የባህልና ታሪካዊ ቅርሶችን በተቀናጀ የመንገድና የእግረኛ መሠረተ ልማት ማገናኘት የከተማዋን የመሠረተ ልማት መስተጋብር (Connectivity) በማሳደግ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች የተሻለ የእንቅስቃሴና የመዝናኛ አማራጭ ፈጥሯል።

የእነዚህ ልማቶች ዋነኛ ዓላማ ዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ማድረግ፣ ለሁሉም እኩል የሆነ የእድል ተደራሽነት መፍጠር፣ የሥራ እድልን ማስፋፋትና አካታች የኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።


ዛሬ አዲስ አበባ እየተጓዘችበት ያለው የልማት ጉዞና ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች የመነቃቃት፣ የመማርና የመለወጥ ተስፋ እየፈጠረ ነው።

ይህም አዲስ አበባ የአፍሪካውያን የጋራ መዲና ብቻ ሳትሆን፣ የዘመናዊ ከተማ ልማት፣ የሥልጣኔ፣ የአካታችነትና የዘላቂ እድገት ማሳያ እየሆነች መምጣቷን ያረጋግጣል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ ነው 

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...

Sep 30, 2026

ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያየን ነው- ሸማቾችና ነጋዴዎች

ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...

Sep 28, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው ናቸው

ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...

Sep 23, 2026

በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መጥቷል

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ተግባራዊ የተደረገው የሩዝ ልማት ኢኒሼቲቭ ውጤታማ እየሆነ መምጣቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት...

Sep 4, 2026