🔇Unmute
ሐረር፣ ሕዳር 2/2019 (ኢዜአ)፡-በሐረሪ ክልል ክህሎት መር እና ገበያ ተኮር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆናቸውን ተገለጸ።
በሐረሪ ክልል ክህሎት መርና ገበያ ተኮር የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን በማስፋፋት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማጉላት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።
በተለይም የወጣቶችንና የሴቶችን የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማበረታታት የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎችን የማመቻቸት፣ የብድር እንዲሁም የገበያ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የክህሎት ሥልጠናዎች እንዲያገኙ ተደርጓል።
ይህም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን አቅም በማጠናከር ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለሥራ ፈጣሪዎች የመስሪያ ቦታ ማመቻቸት፣ የብድር አቅርቦትና የገበያ ትስስር በመፍጠር ያመጣውን ውጤት በማስመልከት ኢዜአ ተጠቃሚዎችን አነጋግሯል።

በከተማዋ በዶሮ እርባታ ዘርፍ የራሳቸውን ሥራ ከፈጠሩ ወጣቶች መካከል ታጅር ኢብራሂም እንዳለው፤ ሥራን ከመጠበቅ ይልቅ በማኅበር በመደራጀት በዶሮ እርባታ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ሀብት ማፍራት ችሏል።
የዶሮ እርባታ ሥራውን ከመንግሥት በተመቻቸለት የመስሪያ ቦታና የክህሎት ሥልጠና ታግዞ በማከናወኑ ውጤታማ መሆን እንደቻለ ገልጿል።
ትምህርት የእውቀት መሠረት በመሆኑ ሌሎች ወጣቶችም አካባቢያቸውን በመቃኘት ወደ ሥራ እንዲገቡ ከራሱ ልምድ በመነሳት መክሯል።

በማኅበር ተደራጅተው መንግሥት ባመቻቸላቸው የመስሪያ ቦታና በወሰዱት የ300 ሺህ ብር ብድር በብሎኬት ማምረት ሥራ ከተሰማሩት ወጣቶች መካከል መሐቡባ ሸምሱ ትገኝበታለች።
ሥራውን በትጋት ማከናወናቸው ገቢያቸውን በማሳደግ ተጠቃሚ ከመሆን ባለፈ ለ17 ዜጎችም ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር መቻላቸውን ጠቁማለች።
በመንግሥት ድጋፍ በመንቀሳቀሳቸው የወሰዱትን ብድር በአግባቡ በመመለስ የራሳቸውን ገቢ እያመነጩ እንደሚገኙም አስረድታለች።

ሌላው የሥራ ዕድል የተፈጠረለት ወጣት ነቢል ኢብራሂም በበኩሉ እንዳለው፤ መንግሥት ያመቻቸላቸውን የማምረቻና መሸጫ ስፍራ በመጠቀም በብረታ ብረት ሥራ ተሰማርተው ራሳቸውን እየጠቀሙ ይገኛሉ።
መስኮት፣ በርና ሌሎች የብረታ ብረት ውጤቶችን በማምረትና ለገበያ በማቅረብ በሚያገኙት ገቢ ድርጅታቸውን እያሳደጉና ለተሻለ ሥራ ራሳቸውን እያዘጋጁ መሆናቸውን አመልክቷል።
የሐረሪ ክልል ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ በዳሳ ገመዳ እንዳሉት፤ የሥራ ዕድል ፈጠራው በክህሎት መር አሰራር እንዲመራ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።
በክልሉ ክህሎት መርና ገበያ ተኮር ሰፋፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተው፤ በተለይ ለወጣቱ የሚደረገው ሥልጠና፣ ምዘናና የድጋፍ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026