🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረቷ ማዕከል አድርጋ እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

“ጉዞ ወደ ዘላቂ፣ አይበገሬነት እና ፍትሃዊነት ወደተረጋገጠበት መጻኢ ዘመን” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የታዳጊ ሀገራት ዓመታዊ የእዳ ወለድ ክፍያ ወደ አንድ ትሪሊዮን ዶላር መጠጋቱንና ይህም ከፍተኛ የብድር ወጪ የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅማቸውን እየገደበው መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ይህንን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የብድር መመሪያዎቻቸውን እንዲያሻሽሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት አደጋዎችን ለመተንበይ የሳተላይት መረጃዎችን እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን ለቅድመ ማስጠንቀቂያ እየተጠቀመች እንደሚገኝ አመልክተዋል።
ድጋፍ የሚሹ ወገኖችም በፈጣን ሁኔታ እርዳታ እንዲያገኙ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሆኖም የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎች ውጤታማ የሚሆኑት ህዝቡ አስቀድሞ እርምጃ የሚወስድበት በቂ የፋይናንስ አቅርቦት ሲኖር ብቻ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በመሆኑም ማንኛውም የአየር ንብረት ፋይናንስ ቃል ኪዳን ምን ያህል? እስከ መቼ? በምን አሰራር? የሚሉትን ሦስት ዋና ዋና ጥያቄዎች ግልጽ በሆነ መንገድ መመለስ እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በአዲስ አበባ በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረቷ ማዕከል አድርጋ እንደምትሰራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኮፕ 32 ጉባኤን በምትዘጋጅበት ወቅት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትና እርምጃዎችን የትኩረ...
Nov 12, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዎች የሀገርን እድገት በማነጽ ረገድ መሰረታዊ ስኬቶችን እያስመዘገቡ መሆኑን ምክትል ጠቅ...
Sep 30, 2026
ቢሻን ጉራቻ፤ መስከረም 15/2019 (ኢዜአ) ፦በቢሻን ጉራቻ ከተማ ለመስቀል በዓል በቂ የእርድ እንስሳት አቅርቦት በመኖሩ በተረጋጋ ሁኔታ እየተገበያዩ መሆናቸው...
Sep 28, 2026
ሐረር፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):-በሐረሪ ክልል በኢንዲስትሪ ልማት፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በኮሪደር ልማት የተከናወኑ ተግባራት ተሞክሮ የሚወሰድባቸው መሆ...
Sep 23, 2026