የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

<p>ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ድርድር ለማጠናቀቅ በቂ ዝግጅት አድርጋለች -ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)</p>

Feb 18, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ለመሆን እያደረገች ያለውን ድርድር ለማጠናቀቅ የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረጓን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ።


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ጨምሮ የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ጋር ተወያይተዋል።


የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ውይይቱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።


በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን የሚደረገውን የድርድር ሂደት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ይዛ እየሰራች መሆኑን በተመለከተ ከዋና ዳይሬክተሯ ጋር ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።


ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ለመሆን ከ23 ዓመት በፊት ድርድር መጀመሩን አስታውሰው፥ እስካሁን አራት የሥራ ላይ ቡድን ውይይቶች ማካሄዷን ተናግረዋል።


የፊታችን መጋቢት በጄኔቫ ለሚደረገው አምስተኛው የሥራ ላይ ቡድን ስብሰባም በቂ ዝግጅት ማድረጓን ተናግረዋል።


በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ሀገራት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን ጠቁመው፥ 18 አንቀጾች ተዘጋጅተው መቅረባቸውንም ገልጸዋል።


አሁን ላይ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከዓለም ንግድ ድርጅት ጋር ድርድር ለማጠናቀቅ የሚያስችል በቂ ዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።


የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026