
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሁለት ሽልማቶችን ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ።
“Aviation Achievement Awards” የተሰኘ የአቪዬሽን ዘርፍ የሽልማት መርሃ ግብር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዱባይ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሽልማቶችን ማግኘቱን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።
የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ እቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Air Cargo Pharma Service of the Year,Africa) እና የአፍሪካ ምርጥ የዕቃ ጭነት አገልግሎት አየር መንገድ (Cargo Airline of the Year,Africa) ያገኛቸው ሽልማቶች ናቸው።
ሽልማቶቹ አየር መንገዱ ለልህቀት፣ ፈጠራ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያመላክቱ ናቸው።
ዓለም አቀፍ የዕቃ ጭነት በረራ አድማስ በማስፋት በዓለም ደረጃ ያለውን ተፎካካሪነት አጠናክሮ እንዲቀጥል አበርክቶ እንዳለውም ገልጿል።
የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት መዳረሻዎቹንና አገልግሎቶቹን በማስፋፋት የመሪነት ሚናውን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አየር መንገዱ በመረጃው አመልክቷል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026