የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በዲጂታል ስርዓቱ ከፍተኛ ውጤት አስገኝቷል-ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

Jul 3, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24/2017 (ኢዜአ)፦ባለፉት አምስት አመታት ሲተገበር የቆየው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በዲጂታል ስርዓቱ ውጤት አስገኝቷል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ማረጋገጥ የሚቻለው የአሰራር ስርዓትን በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በኢኖቬሽን ሲደገፍ ነው።

ኢትዮጵያም ወደ ዲጂታል ስርዓት መግባት የሚያስችላትን የህግ ማዕቀፍ እንዲሁም ስትራቴጂ በማዘጋጀት ወደ ስራ እንደገባች ገልጸዋል።

በተጨማሪም ወደ ዲጂታል ስርዓቱ መግባት የሚያስችሉ መሰረተ ልማቶች ተሟልተው ተግባራዊ መደረግ መጀመራቸውን አስታውቀዋል።

ስትራቴጂው ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና የ10 አመት መሪ የልማት ዕቅድ ስትራቴጂዎች እንዲሁም ከአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ጋር ተሳስሮ ሲተገበር መቆየቱንም ገልጸዋል።

ባለፉት አመታት ተግባራዊ ሲደረግ የቆየው የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚጠናቀቅ ገልፀው በቀጣይ 2030 ድረስ ተግባራዊ የሚደረገው የ5 አመት ስትራቴጂ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ ነው የጠቀሱት።

ባለፉት አምስት አመታት ሲተገበር የቆየው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፉ ላይ አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡቡት ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

ባለፉት አምስት አመታት የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት በመዘርጋት፣ የዲጂታል አገልግሎት በማስፋት እንዲሁም የዲጂታል መታወቂያ ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው አንስተዋል።

የመንግስትን የአሰራር ስርዓት ከማዘመን ጋር በተያያዘ የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን እውን ለማድረግ ከተሰሩ ስኬታማ ስራዎች መካከል መሆኑን ገልፀዋል።

ማዕከሉ በአንድ ጣራ ስር የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ክልል ከተሞች በማስፋት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026