
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ የሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን በጥራትም በስፋትም ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ገለጹ።
የኮምቦልቻ ተርሚናል በተያዘው በሐምሌ ወር መጨረሻ እንደሚመረቅ ተመላክቷል።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በኢትዮጵያ ትልቁን የአየር ትራንስፖርት የሚሰጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ላይ በ22 ከተሞች የበረራ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም በአፍሪካ ትልቅ አገልግሎት መሆኑን ጠቁመዋል።
አገልግሎቱ አሁንም በቂ አለመሆኑን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ደረጃውን በጥራትም ሆነ በስፋት ለማሳደግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ከእነዚህም መካከል መንገደኞች የሚስተናገዱባቸው ተርሚናሎች ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ረገድ በበርካታ ኤርፖርቶች ከፍተኛ ስራ መሰራቱን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የአዳዲስ የተርሚናሎች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው የኮምቦልቻ ተርሚናል ግንባታ ስራም በተያዘው የሐምሌ ወር መጨረሻ እንደሚመረቅ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በሽሬ፣ ነቀምት እና ደምቢዶሎ አዳዲስ ተርሚናሎች ለመገንባት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል።
ነባር የአውሮፕላን መንደርደሪያዎችን በማደስ ትልልቅ አውሮፕላኖችን ማስተናገድ በሚችሉበት ደረጃ ከፍ የማድረግ ስራዎችም እየተሰሩ መሆኑን አመላክተዋል።
ምንም ኤርፖርቶች ባልነበሩባቸው አካባቢዎችም ስድስት ኤርፖርቶች እየተገነቡ መሆናቸውንም ነው ዋና ሥራ አስፈፃሚው የገለጹት።
ከእነዚህም መካከል የያቤሎ ኤርፖርት በነሐሴ ወር እንደሚመረቅ ተናግረዋል።

አየር መንገዱ የሀገር ውስጥ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎትን በጥራትም ሆነ በስፋት ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025