
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ የ2018 በጀት ዓመት የማንሰራራት ጉዟችንን የሚያፀኑ አዳዲስ እመርታዎችን ለማስመዝገብ በጋራ የምንተጋበት ዓመት ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገተለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን እንደመነሻ በመውሰድ በተዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የ2017 በጀት ዓመት በብዙ መልኩ የኢትዮጵያ የብልጽግና ታሪክ እጥፋት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓመቱ እውነትም የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆነ ዓመት ነበር ብለዋል።

የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድም እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።
በበጀት አመቱ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማድረግ የከረሙ ስብራቶቻችን ጠግነናል ሲሉም አክለዋል፡፡
የሕዳሴ ግድብን አጠናቅቀናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋዝ ፕሮጀክታችንንም እያጠናቀቅን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡
በከተሞቻችን የጀመርናቸው የኮሪደር ልማቶች ውጤት ማምጣት ጀምረዋል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የገጠር ኮሪደርም ጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል።
የ2018 በጀት ዓመት ግቦቻችን እነዚህን መልካም አፈጻጸሞች መነሻ የሚያደርጉ፣ ካለፈው በላይ ትጋትና ጥረት የሚጠይቁ ናቸው ሲሉም አስገንዝበዋል።
ለብቻ መሮጥን ብቻ ሳይሆን ጠንካራ ቅንጅትንም ይፈልጋሉ ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬ በእኛ እጅ ናት ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ በጀት ዓመት የላቁ ድሎችን በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ማንሠራራት የሚያውጀው ትውልድ አካል እንደሆንን በማመን ለበለጠ ስኬት በትጋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026