የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የዩኒቨርሲቲ - ኢንዱስትሪ ትስስር የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ያጎለብታል - ምሁራን

Oct 23, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረማያ፤ ጥቅምት 10/2018(ኢዜአ)፦ የዩኒቨርሲቲ - ኢንዱስትሪ ትስስር የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲጎለብት በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያበረክት መሆኑን ምሁራን ገለጹ።

የምስራቅ ኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ምስረታ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።

በምክክሩ መድረክ ላይ የተሳተፉት ምሁራን ለኢዜአ እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲ - ኢንዱስትሪ ትስስር የምርምር ቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲጎለብት ፋይዳው የላቀ ነው።


በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪ ትስስር አስተባባሪ ፈይሳ ሁንዴሳ እንዳሉት፤ ትስስሩ ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲዎችና - ኢንዱስትሪዎች በተበጣጠሰ መንገድ የሚያከናውኑት ስራዎችን ወጥ እንዲሆን የሚያስችል ነው።

ትስስሩም የዩኒቨርsiቲ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የቀሰሙትን እውቀት በኢንዱስትሪዎች የተግባር ልምምድ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል።


ትስስሩ ኢንዱስትሪዎች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት ከዩኒቨርሲቲዎች ስልጠና፣ ማማከርና የምርምር ቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲያገኙ ያስችላል ያሉት ደግሞ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር እሸቱ መኮንን(ዶ/ር) ናቸው።


በኦዳ ቡልቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት እና አጋርነት ዳይሬክተር ጥምቀተ ዳኜ(ዶ/ር) በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲ - ኢንዱስትሪ ትስስር ሀገራዊ የልማት እቅዶችን በጋራ ለማሳካት እገዛ ያደርጋል።

እንዲሁም የማህበረሰብ ችግሮችን በቅርበት ለመፍታትና የጋራ ችግሮችን አቅዶ በጋራ ለመቅረፍ ብሎም መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አክለዋል።



ትስስሩ ዩኒቨርሲቲዎችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር በማስተሳሰር በተግባርና ንድፈ-ሃሳብ የዳበረ የሰው ሃይል ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ዋና ስራ አስኪያጅ አህመድ ረሺድ ናቸው።

በፎረም ምስረታው የምክክር መድረክ ላይ የሐረማያ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ ጅግጅጋ፣ ኦዳቡልቱምና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች፣ የትምህርት ሞያ ስልጠና ኮሌጆች እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የመንግስት እና የግል ኢንዱስትሪ ተወካዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026