🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 20/2018 (ኢዜአ):- የገጠሩን ማህበረሰብ ኑሮ የመቀየር እና ምርታማነትን የማሳደግ ተግባር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ባጠረ ጊዜ ማሳካት የሚያስችል መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ትናንት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የክረምት ስንዴ ምርት አሰባሰብን ጎብኝተው የበጋ ስንዴ እርሻ ሥራን ማስጀመራቸው ይታወቃል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት የገጠሩን ማህበረሰብ ኑሮ የመቀየር ስራ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ባጠረ ጊዜ ማሳካት የሚያስችል ነው ብለዋል።
መንግስት ከተሞችን የመቀየር እና ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ እንዲሁም የስራ ዕድል ፈጠራን ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት በርካታ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ ወደ ስራ መግባቱን አንስተው በኢትዮጵያ አብዛኛው ማህበረሰብ የሚኖረው በገጠር ክፍል መሆኑንና መንግስት በገጠር የሚኖሩ ዜጎችን ኑሮ ለመቀየር እና ምርታማነት ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል በአትክልት፣ ፍራፍሬና ሰብል እጅግ አበረታች ውጤት መገኘቱንና የምስራቅ ሸዋ ዞን የስንዴ ምርት ስራ የሚያመላክተው ይህንኑ ነው ብለዋል።
በዞኑ ያለው የኩታ ገጠም የስንዴ እርሻ በኮምባይነር እየታጨደ መሆኑን በማንሳት ይህም ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ እንደሆነ ነው አፈ ጉባኤው የገለጹት።
ኢትዮጵያ ስንዴ፣ ሩዝ እና አቮካዶን ጨምሮ በተለያዩ ምርቶች ራሷን ለመቻል እያከናወናቸው ያለው ስራ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበበት መሆኑን አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ስንዴ ከመግዛት ተላቃ በራሷ የማምረት አቅም ማሳደጓ የዚሁ ስራ ማሳያ ነው ብለዋል።
የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ በመቀጠል በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጉዞ ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል በገጠር ትራንስፎርሜሽን እየተከናወነ ያለው ስራ በሌሎች ክልሎችም እየተከናወነ መሆኑን በመጥቀስም ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ያለው ስራ ውጤታማ መሆኑን አመልክተዋል።
የገጠሩን ክፍል ለመቀየር እየተከናወነ ያለው ስራ እጅግ ተስፋ የሚሰጥና አበረታች መሆኑንና ተደራሽነቱን በማስፋት የኢትዮጵያን ብልጽግና በአጠረ ጊዜ እንደሚሳካ አያጠራጥርም ነው ያሉት።
የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...
Jun 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...
Jun 1, 2026
አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...
May 25, 2026
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026