🔇Unmute
ሀዋሳ ፤ ሕዳር 17/2018 (ኢዜአ)፦ የንብ በማነብ ስራቸውን በማዘመን ከምርቱ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን በሲዳማ ክልል የዳራ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
በሲዳማ ክልል የዳራ ወረዳ አርሶ አደር ትግሉ ዮሐንስ የንብ ማነብ ሥራቸውን ውጤታማ በማድረግ የማር ምርታማነታቸውን በማሳደግ ከቤት ፍጆታ አልፈው ለገበያ በማዋል የገቢ ምንጫቸው ማደጉን ተናግረዋል፡፡
በአሥር የንብ ቀፎዎች የጀመሩትን የንብ ማነብ ሥራን በማሳደግም በአሁኑ ወቅት ከ100 በላይ ቀፎዎች ላይ ማድረሳቸውን አስረድተዋል፡፡
ከዚህም በዓመት ከ500 ኪሎ ግራም በላይ ማር አምርተው ለገበያ በማዋል ገቢያቸውን ማሳደጋቸውን ገልፀዋል፡፡

ከማር ምርቱ ባለፈ ንግስት ንቦችን በማባዛት ለሌሎች አርሶ አደሮች በማከፋፈልም ተጠቃሚ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡
የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር እሸቱ አርገታ በበኩላቸው፤ ከ30 በላይ ቀፎዎችን ንብ በማነብ በዓመት ከ200 ኪሎ ግራም በላይ በማምረት ተጠቃሚነታቸው መጨመሩን አስረድተዋል ፡፡
የወረዳው እንስሳት ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ሲርባሞ በበኩላቸው፤ በወረዳው በንብ ማነብ ለሚሰማሩ አርሶ አደሮችና ኢንተርፕራይዞች አጫጭር ሥልጠናዎችን ማመቻቸት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ በተጨማሪም የቀፎ አቅርቦትና ለማር ምርት የተመረጡ አበቦችን እንዲተክሉ መሰራቱን አስረድተዋል፡፡
በሲዳማ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን ጃንጄ፤ በክልሉ 100 መንደሮችን በንብ ማነብ ማደራጀት እንደተቻለ ጠቅሰዋል ፡፡
የማር ምርታማነቱን ውጤታማ ለማድረግም በዘርፉ ለሚሰማሩ አርሶ አደሮችና ለሌሎች አካላት ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የቀፎና ሌሎች ግብዓቶችን አቅርቦት ለማሳደግም ከ150 ሺህ በላይ ቀፎዎችን ለማሰራጨት ከታቀደው ውስጥ እስካሁን ከ40 ሺህ በላይ ማሰራጨታቸውን አብራርተዋል፡፡
ከዚህም 3 ሺህ 355 ቶን ማር ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደስራ መገባቱን አስረድተዋል፡፡
የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ አርሶ አደሩ የገበያ አማራጭ እንዲያገኝ በማህበር በማደራጀት በይርጋ ዓለም የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ለሚገኙ ኩባንያዎች እንዲያቀርቡ ለማድረግ ሥራዎች መጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...
Jun 4, 2026
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...
Jun 1, 2026
አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...
May 25, 2026
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...
May 15, 2026