🔇Unmute
ደብረብርሃን፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ የደብረ ብርሃን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተኪና የውጭ ምንዛሬን የሚያስገኙ ምርቶችን በስፋት በማምረት የሀገሪቱን እድገት ለማፋጠን የድርሻውን እየተወጣ መሆኑን አስታወቀ።
የልዩ ኢኮኖሚ ዞኑ ሥራ አስኪያጅ የሺጥላ ሙሉጌታ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ ካሉ ስምንት ሼዶች መካከል በስድስቱ ኢንዱስትሪዎች ገብተው በማምረት ላይ ይገኛሉ።
ቀሪዎቹን በቅርቡ ለባለሀብቶች ለማሸጋገር እየተሰራ ነው ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ አራት ወራት የተመረተ ከ7 ነጥብ ሁለት ሚሊዮን በላይ የአሜሪካን ዶላር ግምት ያለው የቢራ ብቅል ለፋብሪካዎች መቅረቡን አስታውቃል።

በኢኮኖሚ ዞኑ በሚገኘው ቡርቱማልት የብቅል ፋብሪካ ተመርቶ ለቢራ ፋብሪካዎች በማቅረብ ከውጭ የሚገባን በመተካት የውጭ ምንዛሪ መዳን መቻሉ ተናግረዋል።
እንዲሁም በልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተመርተው ወደ ውጭ ከተላኩ የጨርቃጨርቅና አልባሳት 676ሺህ 523 የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ተኪ ምርት በማምረትና የአርሶ አደሩን ምርት በግብአትነት በመጠቀም የገበያ ትስስር በመፍጠር አስተዋጽኦ ማበርከታቸውንም አንስተዋል።
ከሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ከአርሶ አደሮች ጋርም የገበያ ትስስር መፈጠሩን ጠቅሰዋል።
የደብረ ብርሃን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ተኪ እና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ምርቶችን በስፋት በማምረት የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በኢኮኖሚ ዞኑ ከሚሰሩ ኢንዱስትሪዎች መካከል በሻንግ ቼንግ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሰው ሀብት ተቆጣጣሪና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ባለሙያ ወጣት ውብሸት ሳፋቶ እንዳለው፤ ፋብሪካው ምርቱን በጥራት እና በብዛት በማምረት ወደ ውጭ እየላከ ይገኛል።
ሀይማኖት ብርሃኑ በበኩላቸው ከሁለት ዓመት በላይ በፋብሪካው ተቀጥረው በመስራት የተሻለ የስራ ልምድና ክህሎት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
በደብረ ብርሃን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በአሁኑ ወቅት ከ3ሺህ በላይ ሰዎች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ተመልክቷል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026