የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የግብርና ሜካናይዜሽን የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

Nov 28, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ የግብርና ሜካናይዜሽን አዳዲስ የአመራረት ዕድሎችን በማስፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ(ዶ/ር) ገለጹ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ(ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ የግብርና ሜካናዜሽን ስርዓት የዘርፉን ምርታማነት በማዘመን ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

በመንግስትና በግሉ ዘርፍ አጋርነት ዘርፉን ለማዘመንና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በርካታ ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።


ኢንስቲትዩቱ በሚያከናውናቸው የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በመታገዝ የዘርፉን ምርታማነት በማሻሻል ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

የምግብ ሉዓላዊነትን ዘላቂና ወጥ በሆነ መልኩ ለማረጋገጥ ከምርት እስከ ገበታ ያለውን ሂደት የሰመረ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የሜካናይዜሽን ግብርናን ማስፋፋት፣ ምርታማነትን ለማሳደግና ጥራት ያላቸውን የግብርና ውጤቶች በስፋት ለማምረት አቅም እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

የግብርና ሜካናይዜሽን አዳዲስ የአመራረት ዕድሎችን በማስፋት የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል።

ኢንስቲትዩቱ ዘመናዊ ትራክተሮችንና ኮምባይነሮችን ለአርሶ አደሮች በስፋት ተደራሽ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ተግባራት ማከናወኑንም ጠቅሰዋል።


በዚህም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ጨምሮ በሌሎች ምርቶች ላይ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባለሃብቶች የእርሻ መሳሪያዎችን በብዛት ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለአርሶ አደሮች ተደራሽ እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

በቀጣይ የእርሻ መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ለአርሶ አደሮች በግዥና በኪራይ ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026