🔇Unmute
ገንዳ ውኃ፤ ህዳር 19/2018(ኢዜአ)፦ ለበጋ መስኖ ልማት የሚያስፈልጉ የግብርና ግብአቶችን በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን የሕብረት ሥራ ማህበራት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የመተማ ገበሬዎች ሕብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ከሰባት ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የአፈር ማዳበሪያ ለመስኖ ልማቱ እያቀረበ መሆኑም ተመሏክቷል።
የጽህፈትቤቱ ኃላፊ ተወካይ ሲሳይ አለበል እንደገለጹት፣ዞኑ ለመስኖ ልማት የሚውል ሰፊ መሬት፣ ለበጋ መስኖ ልማት የሚስማማ የአየር ንብረትና ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ ወንዞች ባለቤት ነው።
በመሆኑም ይህን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ለበጋ መስኖ ልማት አስፈላጊ ግብአቶችን በማቅረብ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በልማቱም የአርሶ አደሩን ዘላቂ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመረው የግብአት አቅርቦት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በመስኖ የሚሳተፉ አርሶ አደሮች በየዓመቱ የግብዓት እጥረት ይገጥማቸው እንደነበር አስታውሰው፣ ዘንድሮ ችግሩን ለመፍታት በተደረገው ጥረትማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ ፀረ ተባይና ኬሚካል ቀድሞ መቅረቡንአቶ ሲሳይ ተናግረዋል።
በመተማ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን የቀረበው ማዳበሪያም በበጋ መስኖ ልማት የሚሳተፉ አርሶ አደሮችን ምርታማነት በማሳደግ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት የሚያስችል ነው።
የመተማ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየኑ ሥራ አስኪያጅ ሀብቴ ዘውዱ በበኩላቸው የበጋ መስኖ ልማትን በግብአት በመደገፍምርታማነትን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሰራ ነው።
ለዚህም በተያዘው የበጋ ወቅት ለሚካሄደውየመስኖ ልማት ዩኒየኑ 2ሺህ 800 ኩንታል ዳፕ እና ዩሪያ ማዳበሪያ ማቅረቡን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
በገንዳውኃ ከተማ ዙሪያ በመስኖ ልማት የተሰማሩት አርሶ አደር አብዱ ሁሴን እንደገለጹት በልማቱ በየዓመቱ ይገጥማቸው የነበረው የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት መፈታቱን ገልጸዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026