🔇Unmute
አምቦ፤ህዳር 29/2018(ኢዜአ)፦የአምቦ-ወሊሶ ኮንክሪት አስፋልት መንገድ ግንባታ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ገለጸ።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አምቦ አካባቢ ፕሮጀክት ማኔጅመንት ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኜ ለገሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ከስድስት አመት በፊት ተጀምሮ ግንባታው የዘገየው የመንገዱ ግንባታ አሁን ላይ እየተፋጠነ ነው።

ከ 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እየተከናወነ ያለው የመንገዱ ግንባታ 63 ነጥብ 78 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን መሆኑንም ተናግረዋል።
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እየተከናወነ ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እያከናወነው ይገኛል ብለዋል።
መንገዱ በሁለቱ ከተሞች መካከል ያለውን ግንኙነት እና የንግድ እንቅስቃሴ ከማሳለጡም የአካባቢው ነዋሪዎችም ምርታቸውን በቀላሉ ለገበያ እንዲያቀርቡ ያግዛልም ነው ያሉት።

ቀሪ የመንገድ ግንባታ ስራዎቹንም በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአምቦ-ወሊሶ መንገድ ስራ አስኪያጅ አቶ ሺበሺ ጫካ፤ የመንገዱን ግንባታ ፈጥኖ በማጠናቀቅ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የአምቦ-ወሊሶ መንገድ ግንባታ በአጭር ግዜ ለማጠናቀቅ ደቡብ ምዕራብ ሸዋንና ምዕራብ ሸዋን ከማገናኘት አልፎም የወንጪና የደንዲ ኢኮ ቱሪዝም ሎጆች ለሚደረጉ ጉዞዎችም ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።
ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ የመንገዱ መጠናቀቅ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

በተለይም ወላድ እናቶችን ወደ ጤና ተቋማት ፈጥኖ ለማድረስ አስቸጋሪ እንደሆነ ጠቅሰው መንገዱ ሲጠናቀቅ ችግራቸውን የሚያቃልል በመሆኑ የመንገዱን መጠናቀቅ በጉጉት እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል።
ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...
Aug 28, 2026
መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...
Aug 18, 2026
ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...
Aug 10, 2026
አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...
Jul 20, 2026