የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ መርሃ ግብር ለዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ገንቢ ሚና እየተጫወተ ነው

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ መርሃ ግብር በህዝብና ተቋማት መካከል መተማመን በመፍጠር ለዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ገንቢ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም አስታወቀ።

የፕሮግራሙን ተቋማዊ አሰራርና ውጤታማነት ለማሳደግ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ በአዋጅ 1284/2015 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

አዋጁ ነዋሪዎች የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ፣ ሌሎች መብቶቻቸውን የመጠቀም እድላቸውን ለማስፋት፤ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባይ መካከል በሚኖር ግንኙነት እምነት እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና የተሳለጠ አሰራር ለመዘርጋት ያለመ ነው።


በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የባለድርሻ አካላትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሳሚናስ ሰይፉ ለኢዜአ እንደተናገሩት ዲጂታል ኢትዮጵያን በማሳለጥ ማጭበርበርን ከማስቀረት በተጨማሪ በህዝብና በተቋማት መካከል መተማመንን ለመፍጠር ዲጂታል መታወቂያ ጉልህ ሚና አለው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳና በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ 2030 ውስጥ አንዱና ዋናው አስቻይ ምሰሶ መሆኑን ተናግረዋል።

ለተለያዩ ዘርፎች አገልግሎት ለመስጠት አስቻይ ሁኔታን መፍጠር፤ ተደራሽነትን ማረጋገጥ እና ለዲጂታል የህዝብ መሰረተ ልማት መሰረት በመጣል በኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽንን ለማሳካት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

እስካሁን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ያደረጉ ሰዎች ቁጥር 29 ሚሊየን መድረሱንም ጠቅሰዋል።

በፕሮግራሙ የተቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ለሚያሟሉ ነዋሪዎች ባለ 12 አሃዝ ልዩ የፋይዳ መለያ ቁጥር እየተሰጠ እንደሚገኝና ይህ መለያ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ ባለቤት ተደርገው እንደሚቆጠሩ አስረድተዋል።

በምዝገባ ሂደቱ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ህዝቡ በንቃት እንዲሳተፍን ጥሪ አቅርበዋል።

የዲጂታል መታወቂያ ከተቋማት ጋር መተሳሰሩ የአገልግሎቱን ተጠቃሚ ቁጥር ለማሳደግ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026