የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ትግበራ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ በህጋዊ እና ትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ተችሏል

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ በውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ትግበራ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ በህጋዊ እና ትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ተችሏል ሲሉየብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የገንዘብ ፖሊሲን የማዘመን፣ የውጭ ምንዛሬ የማሻሻል ፣የፋይናንስ ዘርፍ ለውጥ እና የተቋማዊ ማሻሻያ ስራዎች ከተከናወኑ ዋና ዋና የማሻሻያ ተግባራት መካከል ተጠቃሽ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

እነዚህ የማሻሻያ ተግባራት የዋጋ ግሽበትን በሰኔ 2012 ከነበረበት ከ30 በመቶ በታህሳስ 2018 ላይ ወደ 9.7 በመቶ ለመቀነስ አስችለዋል ብለዋል።

በውጭ ምንዛሬ ማሻሻያ ትግበራ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከማሳደግ ባለፈ በህጋዊ እና ትይዩ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ ተችሏል ነው ያሉት።

አሁን ላይ ለግሉ ዘርፍ የሚቀርብ የብድር ድርሻ 77% መድረሱንም አስታውቀዋል። ዲጂታል አካውንቶችን በተመለከተም 254 ሚሊዮን አካውንቶች ማድረስ ያስቻለ ማሻሻያ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎‎በቀጣይ የዋጋ ንረትን በነጠላ አሃዝ እንዲቆይ ማድረግ፣ የውጭ ምንዛሬ ገበያውን የበለጠ ተገማች እና የተረጋጋ ማድረግ፣የባንኮች ውህደት እና ግዢ ተግባራዊ ማድረግ፣ የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚመራ ተቋምን ማደራጀት፣ የወለድ ነጻ የባንኪንግ ስርዓትን ማጠናከር ትኩረት ከሚደረግባቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸውን መናገራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026