የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በልማት አርበኝነት የአዲሱ ዘመን የዓድዋ ድሎችን እያስመዘገብን ነው - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን ብልፅግና የሚያረጋግጡ የአዲሱ ዘመን የዓድዋ ድሎችን በልማት አርበኝነት እያስመዘገብን ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የዓድዋ ድል ለሠራዊታችን የሁልጊዜም የድል ስንቅ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የዓድዋ ድል የዓለም ጥቁር ህዝቦችና የአፍሪካውያን ታላቅ የጀግንነትና የነጻነት ቀንዲል ነው ብለዋል።


በዓሉ "ከአኩሪ ታሪክ፣ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ ሲከበርም ቀደምት ጀግኖች የተቀዳጁትን አኩሪ ታሪክ በልማት አርበኝነት ለመድገም ቃል በመግባት መሆኑን ገልጸዋል።

የዓድዋ ድል ትዕምርት ኢትዮጵያውያን የውስጥ ልዩነቶች ሳይበግሯቸው በሀገር ጉዳይ በጋራ መቆም እንደሚገባቸው በተግባር ያረጋገጠ መሆኑንም ተናግረዋል።

ቀደምት ጀግኖች በደምና አጥንታቸው በዓድዋ ሰንሰለታማ ተራሮች የተቀዳጁት አኩሪ ጀብዱ የማትበገር ኢትዮጵያን ለትውልድ ማስረከብ እንዳስቻለ አንስተዋል።

የዚህ ዘመን ትውልድም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ዘብ በመቆም እንደዓድዋ ጀግኖች የራሱን የድል ታሪክ መፃፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በዚህም በልማት አርበኝነት ኋላቀርነትን፣ ድህነትንና መከፋፈልን በማስቀረት የኢትዮጵያን ብልጽግና በማረጋገጥ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስተላለፍ የታሪክ አደራ እንዳለበት አስረድተዋል።


እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች፣ የስንዴ አብዮት ስኬት፣ ከአረንጓዴ ዐሻራ እስከ መዲናችን አዲስ አበባን እንደስሟ ውብ የማድረግ የትራንስፎርሜሽን ስራዎች ሁሉ የአዲሱ ዘመን የዓድዋ ድሎቻችንና ለቀጣዩ ትውልድ ውርስ ናቸው ብለዋል።

ዓድዋ ትልቅ የአርበኝነት ትምህርት ቤት ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ ኢትዮጵያን በአንድነት ወደማይቀረው ብልፅግና ለማድረስ የምናደርገው ጉዞ በሚታዩና በሚጨበጡ የለውጥ ፍሬዎች የታጀበ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዘመናችን ታላላቅ ድርብ ታሪኮችን ሰርተን ለማለፍ እንነሳ ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሚያዝያ እና ግንቦት የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት ከምስል ጋር!

  የኢንዱስትሪ መስፋፋት እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ነጻነት ለማረጋገጥ፣ የረጅም ጊዜ የኢን...

Jun 4, 2026

በዲጂታል ክህሎት ራሳችንን እያበቃን ነው - ተማሪዎች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 20/2018(ኢዜአ)፦ በአምስት ሚሊየን የኢትዮ-ኮደርስ መርሃ ግብር በመታገዝ በዲጂታል ክህሎት ራሳቸውን እያበቁ መሆናቸውን አስተያየታቸውን...

Jun 1, 2026

በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ የአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት ተሰጥቷል

አዳማ፤ግንቦት 16/2018(ኢዜአ)፦በክልሉ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍ ለአሰራር ማሻሻያና ለተቋማት ግንባታ ትኩረት መሰጠቱን በብልፅግና ፓርቲ የኦ...

May 25, 2026

በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው

ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ከተረጅነት የመውጣት ጥረትን ለማሳካት የሚያስችል ተጨባጭ ውጤት እያመ...

May 15, 2026