የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር መሰማራታችን ሃብት ለማፍራት አስችሎናል-ተጠቃሚዎች

Mar 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረብርሃን ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦በሌማት ትሩፋት መርሐግብር መሰማራታቸው ሀብት ለማፍራት እንዳስቻላቸው በሰሜን ሸዋ ዞን በእንስሳት ሃብት ልማት የስራ እድል የተፈጠረላቸው ማህበራት አስታወቁ።

የቡና ወጪ ንግድን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ለተቀናጀ ጥረት ትኩረት ተሰጥቷል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርን ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

የመርሃ-ግብሩ ዋነኛ ግብ፤ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ እና የምግብ ስርዓትን ማሻሻልን ያለመ ነው።

በዚህም መሰረት በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች ዜጎች በስጋ፣ በእንቁላል፣ በማር እና በወተት አምራችነት በስፋት በመሳተፍ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።

በአንጎለላና ጠራ ወረዳ በጎልባና ቃፌሮ ቀበሌ ሽመልስ ሙሉጌታና ጓደኞቹ የዶሮ እርባታ ማህበር ሰብሳቢ ዳዊት ሀይሌ፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ከስራ አጥነት ወደ ስራ ፈጣሪነትና ባለሀብትነት እንድንሸጋገር አድርጎናል ሲል ነው የገለጸው።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በሶስት ጫጩቶች የተጀመረው ስራ በአሁኑ ወቅት የጫጩቶቹን ቁጥር 6 ሺህ 500 ለማድረስ ችለናል ብሏል።

አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ካፒታል በማስመዝገብ ወደ ባለሃብትነት ለመሸጋገር እየሰሩ እንደሚገኙ ገልጿል።

በዚሁ ወረዳ የቆባ እንስሳት እርባታ ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ፀጋዬ እንደገለጹት፤ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የእንስሳት ዘርፉን ምርታማነትና ልማት ለማሳደግ እያስቻለ ነው።

አሁን ላይ 110 ዝርያቸው የተሻሻለ ላሞችን በመንከባከብ በቀን እስከ አንድ ሺህ ሊትር ወተት በማምረት ለአቀነባባሪዎች እያስረከቡ መሆናቸው ገልጸዋል።

ዘርፉን ለማዘመንና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ በተደረገላቸው እገዛም በሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር ወጪ ግዥ መፈፀማቸውን ነው የገለጹት።

ከስደት መልስ ከጓደኞቿ ጋር በመደራጀት ስራ እንደጀመሩ የምትናገረው ብጽአት ጌታቸው ከመንግስት በተሰጣቸው ቦታ ሼድ በመገንባት የዶሮ እርባታ ስራውን ለማሳደግ እንደቻሉ ነው የምትናገረው።

የዶሮ እርባታ ስራው ላይ በመሳተፍም ሶስት ሚሊዮን ብር የሚሆን ካፒታል በማስመዝገብ ለሌሎች ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር እንደቻሉ ነው የገለጸችው።

የሰሜን ሸዋ ዞን እንስሳትና ዓሳ ሃብት መምሪያ ኃላፊ አቶ ምትኩ ማሙሻ በበኩላቸው፤ በዞኑ በሌማት ትሩፋት የወተት፣ የእንቁላል፣ የስጋ፣ የማርና የዓሳ ምርትን በማሳደግ ገበያ የማረጋጋት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ሰባት ወራት ተኩል የዓሳ፣ የወተት፣ የእንቁላል እንዲሁም የስጋና የማር ምርት በበቂ ሁኔታ በማምረት ገበያ የማረጋጋት ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ባለፉት 7 ወራት ተኩል ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአንድ ቀን ጫጩቶችን በዘርፉ ለተሰማሩ ወጣቶች ማሰራጨት መቻሉን ጠቁመው በሌማት ትሩፋት ከስምንት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026