🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 24/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የዳያስፖራው ማህበረሰብ በሀገሩ ልማት ላይ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርግበትን ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረ በአሜሪካና ዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ገለጹ።
የኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት እና በዩናይትድ ኪንግደም የበርኒንግሃም የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አመራር አባላት ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በቆይታቸውም የኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስፋት ለአገር ዕድገት አቅም እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኢትዮ-አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ኤልያስ ወልዱ በበይነ-መረብ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የተመዘገቡ የልማት ስኬቶች ዕድገትን በማፋጠን የዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው።

የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች መስፋትም በውጭ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በአገራቸው የሚኖራቸውን የልማት ተሳትፎ በማሳደግ አይነተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
በውጭ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላትም በኢትዮጵያ የተፈጠረውን ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች የማስተዋወቅ ስራ እየሰሩ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህም በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በአገራቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማየት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ከአገር ውስጥ አልፎ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን የሚያፋጥኑ ትላልቅ የልማት ለውጦች መምጣታቸውን አስረድተዋል።
በሚቀጥለው ሚያዚያ ወርም በአሜሪካን አገር የሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያና ቀጣናው አገራት የፈጠረውን የኢኮኖሚ ትሩፋት የሚያሳይ ሲምፖዚየም በማዘጋጀት ለማስተዋወቅ እየሰሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሚዘጋጀው ሲምፖዚየም ላይ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን በማስተዋወቅ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች በአገራቸው ልማት ላይ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማላቅ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በዩናይትድ ኪንግደም የበርኒንግሃም የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ ምክትል ሊቀመንበር ሄለን በፍቃዱ በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ከተሞች የተፈጠረው ከፍተኛ መነቃቃት የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘው የኢኮኖሚ ማሻሻያም በውጭ አገራት ለዳያስፖራውማህበረሰብ ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት ተሳትፎ ዕድል መፍጠር እንደቻለ ገልጸዋል።
ለዚህም ለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በእንግሊዝና አካባቢው የሚኖሩ ዜጎች በአገራቸው ልማት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የንግድ ምክር ቤት በማቋቋም ጭምር የዳያስፖራው ማህበረሰብ በኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ የሚኖረውን ተሳትፎ የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።
የኢትዮጵያ ከተሞችን ለማሻሻል የተከናወኑ አስደናቂ የኮሪደር ልማት ስራዎችም ዜጎች ዘመናዊ አኗኗር እንዲከተሉ በማስቻል ለአገር ገጽታ ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተሞች የኮሪደር ልማትም ንጹህና ጤናማ አካባቢ በመገንባት ለዜጎች ሁለንተናዊ ልማትና የፈጠራ አስተሳሰብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።
የመንግስትን አገልግሎቶች በዲጂታላይዜሽን ሥርዓት ለማሳለጥ የተፈጠረው አስቻይ ምኅዳርም የንግድና ኢንቨስትመንት መሰናክሎችን በማስቀረት ወሳኝ አቅም መሆኑን አንስተዋል።
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ በኦዲት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በምግብ ዋስትና እና በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ እያከናወነቻቸው ያሉ ተግባራት ለመላው አፍሪካ አገራት ትልቅ አ...
Apr 16, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ለውጡ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶች በመጠገን፣ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ከፍታና ለማህበራዊ ትስስ...
Apr 3, 2026
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025