🔇Unmute
መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የተበሰረበት ዕለት ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ ወደ ስትራቴጂካዊ የልማት ፕሮጀክቶች የተሸጋገረችበት የለውጥ መጀመሪያ ነበር።
ባለፉት ስምንት ዓመታት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ አቅም በተግባር በመተርጎም ረገድ "ሀገራዊ ልክን" ያሳዩ ናቸው።
የለውጥ ዘመኑ ዋነኛው አሻራ ተደርጎ የሚወሰደው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ለማጠናቀቅ የተወሰደው በሳል እርምጃ ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች እና በውስጥ ፈተናዎች ሳይበገሩ የወል እውነትን የገነቡበት ታላቅ ተጋድሎ ነው።
የለውጡ መንግስት የኢትዮጵያውያንን ዓባይን የመግራት የዘመናት ቁጭት ጉልበቱን ሸብረክ ሳያደርግ ከፊት ሆኖ መርቷል።
ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተሰሚነትና ልዕልና ዳግም ያረጋገጠችበት ታላቅ ክስተት ሆኖም ተመዝግቧል።
በሌላ በኩል በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የፈነጠቀው የተስፋ ብርሃን የኢትዮጵያን ከተሞች ከመጪው ዘመን ጋር ለመዋጀት የተጀመሩ ስራዎች እንዲፋጠኑ አቅም ፈጥሯል።

ዛሬ ላይ የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያ ከተሞችን በአዲስ ገጽታ እንዲገነቡ አስችሏል።
የኢትዮጵያ ከተሞች የእግረኛ መንገድን፣ የብስክሌት መስመሮችንና የሕዝብ መዝናኛዎችን በማካተት ለዘመናት ካንቀላፉበት ነቅተዋል።
የቀደመ ምስረታቸውን ከዘመኑ ጋር በሚመጥን አግባብም ስልጣኔን ከፍ አድርገው አፍሪካውያን በአብነት የሚያነሷቸው ምልክቶች ሆነዋል።
በግብርናው ዘርፍም የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ በኩል የተመዘገበው ስኬት ኢትዮጵያን ከልመና ወደ ሰጪነት ያሸጋገረ ድል ሆኗል።
የአፈር ማዳበሪያ ለማምረት የተጀመረው ስራም በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበውን ድል ይበልጥ የሚያጠናክር ይሆናል።

እንደ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ያሉ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ውበት ወደ ሀብትነት ቀይረዋል። እየቀየሩም ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ የአፍሪካ የሳይንስ ማዕከል እየሆነች ነው፤ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ከማቋቋም ጀምሮ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ተሸጋግራለች።
ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ወዲህ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የተገለጡ ብስራቶች ለዜጎች የዘመናት ቁጭት መልስ የሰጡ እና የኢትዮጵያን ታላቅነት ዳግም በዓለም አደባባይ ያሳዩ ናቸው።
እነዚህ የለውጥ እርምጃዎች "ኢትዮጵያን በልኳ" የመግለጥ ግብን ሰንቀው የተከናወኑ ታላላቅ የልማት አሻራዎች ናቸው።
ቦንጋ ፤የካቲት 16/2017 (ኢዜአ) ፡-በቦንጋ ከተማ የተካሄደውን የህዝብ ውይይት የመሩ ከፍተኛ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በከተማው የተለያዩ የልማት ...
Feb 24, 2025
ደብረብርሀን፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ገበያን ለማረጋጋት የሚያግዙ ከአንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገበያ ማዕከላት ግንባታ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 1/2017(ኢዜአ)፡- በሚቀጥሉት አምስት አመታት በወረቀት የሚካሔዱ አሰራሮችን በማስቀረት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ግብይትና አገልግሎት በተሻለ ...
Feb 8, 2025