የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ፤ መጋቢት 24/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ተናገሩ።

ለውጡን ምክንያት በማድረግ በምዕራብ ሸዋ ዞንና በአምቦ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።


በህዝባዊ ሰልፉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት አቶ አወሉ አብዲ፤ በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በእነዚህ ዓመታት በየአካባቢው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፣ በተለይም በኢኮኖሚው ዘርፍ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በግብርናው ዘርፍ ከባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ በመውጣትና በሜካናይዜሽን በመታገዝ ራስን በምግብ ከመቻል ባለፈ ምርትን ለውጭ ገበያ ማቅረብ ተችሏል ነው ያሉት።

በከተማ ልማትም ከተማዎችን በቴክኖሎጂ ከማዘመን ባለፈ የ"አንድ ማዕከል" አገልግሎት በማስጀመር ህዝቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል።

በለውጡ ዓመታት የተመዘገቡ የልማት ስኬቶችን ለማስቀጠል ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ህዝቡ በአንድነት ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል።


የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ በበኩላቸው፤ የለውጡ መንግስት ቀደም ሲል የነበሩ ውስብስብ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ማከናወኑን ገልጸዋል።

ዘንድሮም በ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለህዝብ የገባነውን ቃል አክብረን፣ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አዲስ ቃልኪዳን የምንገባበትና የተጀመሩ ልማቶችን የምናስቀጥልበት ነው ብለዋል።


የአምቦ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃጫሉ ገመቹ፤ በከተማው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም በኋላ በሁሉም የልማት ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎችም በለውጡ ዓመታት በተመዘገቡ የልማት ስራዎች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወጣት ዳግማዊት ቁምላቸው፤ የተገኙ ስኬቶችን በመጠበቅና የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የሀገሪቱን እድገት ለማፋጠን ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።


ሌሎች ወጣቶችም ለሀገራቸው እድገት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርባለች።


አቶ ንጉሴ ጆሮ በበኩላቸው፤ ህብረተሰቡ በአንድነት በመቆም ለሰላምና ለልማት አስተዋጽኦውን ማስቀጠል ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026