የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

የሀገራዊ ለውጡ አዲስ ምዕራፍ - የመንገድ መሰረተ ልማት

Apr 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መጋቢት 24 በኢትዮጵያ የፖለቲካ ውስጥ አዲስ ምዕራፍን የከፈተ የለውጥ ምዕራፍ ጅማሮ ማብሰሪያ ነው።

ለውጡም በፈተናዎች ውስጥ ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚያሻግሩ በርካታ ስኬቶችን በማስመዝገብ ዘልቋል፡፡

ላለፉት 8 የለውጥ አመታት ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የመንገድ መሰረተ ልማት ነው።

በሀረሪ ክልልም ለመንገድ መሰረተ ልማት በተሰጠው ትኩረትና በተከናወኑ ተግባራት የህዝቡን የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር የቀረፉ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።


በተለይም ገጠሩን ከከተማው ጋር በማስተሳሰር በከተማ እና ገጠር ፍትሀዊ የሆነ የመሰረተ ልማት ተደራሽነት እንዲኖር ለማስቻል ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጿል።

በዚህም ወረዳን ከወረዳ ብሎም ገጠሩን ከከተማ ጋር የሚያገናኙ የአስፓልት እና የጠጠር መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

ይህም አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ለገበያ ማቅረብ እንዲችል፤ እንግልትና የምርት ብክነት መቀነሱ ተመላክቷል።

በከተማም የተገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች የትራንስፖርት እንቅስቃሴው የተሳለጠ እንዲሆን ከማስቻል በተጨማሪ የተገነቡ ምቹ የእግረኛ መንገዶች የዜጎችን ደህንነት ከማረጋገጥ ባሻገር ከተማዋን የተሻለ ገፅታ አላብሰዋል።


የመንገድ ፕሮጀክቶቹ ገፅታ ከመቀየር ባሻገር የየአካባቢው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ ማድረጉ ተገልጿል።

የለውጡ መንግሥት ለህዝቡ ቃል በገባው መሰረት ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ ጀምሮ በጥራት እና ፍጥነት ማጠናቀቅ መገለጫው ሆኗል።

እውን የሆኑ ፕሮጀክቶች ጊዜን ብቻ ማእከል ያደረጉ ሳይሆኑ ጥራትን ጨምረው ዘመን ተሻጋሪነትን ማዕከል ተደረገው የተገነቡ ናቸው።


በለውጡ አመታት በመንገድ መሰረተ ልማት የተሰሩ ስራዎችም ህዝቡ ለዘመናት ሲያነሳቸው የቆዩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኝ ያስቻሉ መሆናቸውን ነው ቢሮው ያስታወቀው።

የክልሉ መንግስት ለመንገድ መሰረተ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026