የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ፖለቲካ እና ደህንነት

በአማራ ክልል በከተማ ክላስተር ዘርፍ አመርቂ ስኬቶች ማስመዝገብ ተችሏል

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህር ዳር፤ መጋቢት 30/2018(ኢዜአ) ፦በአማራ ክልል በከተማ ክላስተር ዘርፍ አመርቂ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሃመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

‎በክላስተሩ ተቋማት በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም የውይይት መድረክ ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።


‎በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ አህመዲን መሃመድ (ዶ/ር) በመድረኩ እንደገለጹት፤ አመራሩ ከባለሙያው ጋር ባደረገው ቅንጅት በከተማ ክላስተር ዘርፍ ስኬት ሊመዘገብ ችሏል።

‎ለዚህም ‎በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ የኢንዱስትሪ መንደሮችን በማስፋፋት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና ገጠርን ከከተማ በማስተሳሰር የተገኘ ውጤት መሆኑን አስረድተዋል።

‎ሥራውም ‎በተለይ የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበትን የገለጠ፣ የህብረተሰቡን የሥራ ባህል የቀየረ እና ከተሞችን ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ተመራጭ ያደረገ ነው ብለዋል።

‎‎እንደ አህመዲን (ዶ/ር) ገለጻ ለውጭ ባለሃብቶች ብቻ ተፈቅዶ የነበረው በኢንዱስትሪ መንደሮች ገብቶ የማልማት ሥራ ለሀገር ውስጥ ባለሃብቶችም መፈቀዱ የኢንዱስትሪና የኢንቨስትመንት ዘርፉ እንዲነቃቃ አድርጓል።

‎‎‌በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በኩልም 5 ሚሊዮን ዜጎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጣታቸውን ጠቅሰው በኢትዮ-ኮደርስ በርካታ ወጣቶችና ሠራተኞች የስልጠናው ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

‎‎በቀሪ ወራትም በከተማ ክላስተር ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰራ አመልክተዋል።


‎‎የክልሉ ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ አማካሪ አቶ ሽቤ ክንዴ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በ32 ከተሞች የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ የአረንጓዴ ልማትና የመዝናኛ ስፍራዎችን ያሟላ የኮሪደር ልማት ግንባታ እየተከናወነ ነው።

‎በቀሪው ጊዜም በዕቅድ የተያዘውን በጥራት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ለማብቃት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ህብረተሰቡም በልማቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

የአማራ ከልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ የቻለ ይግዛው፤ የክላስተር ቢሮዎች አሰራራቸውን እንዲያዘምኑና የሚሰጡት አገልግሎት ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።


በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ገበያ ልማት፣ በቱሪዝምና ሌሎች ተቋማት የዲጂታል ቴክኖሎጂ አሰራርን በማስፈን ለህብረተሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ከብልሹ አሰራር የጸዱ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

‎የዲጂታል ትግበራውም የክልሉን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ከማፋጠን ባሻገር ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድግ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

‎‎‎‎‎በውይይት መድረኩ ላይ በክላስተሩ ሥር የሚገኙ ተቋማት ሃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል- ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ነሐሴ 21/2018 (ኢዜአ) ፦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ...

Aug 28, 2026

በኢሉባቦር ዞን በኩታ ገጠም ከለማው የበቆሎ ሰብል የተሻለ ምርት ለማገኘት የእንክብካቤ ስራ ተጠናክሯል

መቱ፤ ነሐሴ 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቦር ዞን በክረምት እርሻ እየለማ ከሚገኘው የበቆሎ ሰብል የላቀ ምርት ለማገኘት የሰብል እንክብካቤና ጥ...

Aug 18, 2026

በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው

ሀዋሳ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማትን በማሻሻል ለሕዝቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆና...

Aug 10, 2026

በክልሉ በበጀት ዓመቱ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል 

አዳማ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ ሰላምና መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ውጤታማ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን የክል...

Jul 20, 2026